1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የመራሒተ-መንግስት አንጌላ ሜርክል ውሳኔ እና የጀርመን ፖለቲከኞች አቀባበል

ሰኞ፣ ኅዳር 12 2009

በጀርመን ፖለቲከኞች ዘንድ ለወራት የዘለቀው ግምት አሁን ትናንት መቋጫ ተበጅቶለታል። የ62 አመቷ የጀርመን መራሒተ-መንግሥት አንጌላ ሜርክል በሚቀጥለው ዓመት በሚደረገው ምርጫ ለውድድር ይቀርባሉ

https://p.dw.com/p/2T226
Angela Merkel
ምስል picture alliance/dpa/C.Rehder

MMT Q&A Angela Merkel to stand for fourth term as chancellor - MP3-Stereo

ለአስራ አንድ ዓመታት ጀርመንን የመሩት እና የካበተ ልምድ አላቸው የሚባልላቸው አንጌላ ሜርክል ከዚህ ውሳኔ ለመድረስ አብዝተው ማሰላሰላቸውን ተናግረዋል። አንጌላ ሜርክል በጎርጎሮሳዊው 2017 ዓ.ም የሚካሔደው ምርጫ እንደ ከዚህ ቀደሞቹ ቀላል እንደማይሆን በትናንትናው ዕለት ተናግረዋል። መራሒተ-መንግስቷ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በጉልህ እየታየ የመጣው ፅንፍ መያዝ አንዱ ፈተናቸው መሆኑን አልሸሸጉም። ለመሆኑ የመራሒተ-መንግስቷን በመጪው ምርጫ የመወዳደር እቅድ የጀርመን ፖለቲከኞች እንዴት ተቀበሉት? ኃሳባቸውንስ ለማሳካት የሚገጥሟቸው ፈተናዎች ምንድን ናቸው?

ይልማ ኃይለሚካኤል

እሸቴ በቀለ

አዜብ ታደሰ