1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

  የትምሕርት ጥራት በአዳጊ አገሮች

ሐሙስ፣ መስከረም 18 2010

በማደግ ላይ የሚገኙ ሐገራት መንግሥታት ሕፃናትና ወጣቶችን በገፍ ትምሕርት ቤት ማስገባታቸዉ «ትምሕርት ቤት ገብቶ ያልተማረ» ትዉልድን ከማፍራት በስተቀር ዕዉቀትን ለማስጨበት እንዳልጠቀመ ሁለት ዓለም አቀፍ ድርጅቶች አስታወቀ።

https://p.dw.com/p/2kuXN
Deutsche Schule in Äthiophien
ምስል DW/Y. Gebreegziabher

(Beri.Brussels) UNESCO & WB berichte - MP3-Stereo

በማደግ ላይ የሚገኙ ሐገራት መንግሥታት ሕፃናትና ወጣቶችን በገፍ ትምሕርት ቤት ማስገባታቸዉ «ትምሕርት ቤት ገብቶ ያልተማረ» ትዉልድን ከማፍራት በስተቀር ዕዉቀትን ለማስጨበት እንዳልጠቀመ ሁለት ዓለም አቀፍ ድርጅቶች አስታወቁ።የተባበሩት መንግስታት የትምሕርት፤የሳይንስ እና የባሕል ድርጅት (UNESCO) እና የዓለም ባንክ በቅርቡ ያደረጉት ጥናት እንዳረጋገጠዉ የአዳጊ ሐገራት መንግስታት  ትምሕርት እናስፋፋለን በማለት ሕፃናትና ወጣቶችን በብዛት ትምሕርት ቤት ማስገባታቸዉ የትምሕርት ጥራትን እያቀጨጩት ነዉ።የአዳጊ ሐገራት ተማሪዎች ተመሳሳይ ደረጃ ላይ ከሚገኙ የበለፀጉ ሐገራት የእድሜ አቻዎቻቸዉ ጋር ሲነፃፀር እዉቀታቸዉ እጅግ ያነሰ ነዉ።ገበያዉ ንጉሴ ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል

ገበያዉ ንጉሴ

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ