1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቼ ጉቬራ 50ኛ የሙት ዓመት 

ሐሙስ፣ መስከረም 25 2010

አብዮተኛው ቼ ጉቬራ በቦሊቪያ ጦር ተገድሎ ከተቀበረ እነሆ 50 ዓመታት ሊሞላው ጥቂት ቀናት ቀሩ። አድናቂዎቹ እና ተከታዮቹ ለተገፉና ለተጨቆኑ የታገለ የነጻነት ፋኖ አድርገው ያስታውሱታል።

https://p.dw.com/p/2lIHy
Che Guevara/Foto - Che Guevara/Photo/1965 - Guevara Serna, Ernesto, dit Che Guevara
ምስል picture-alliance/akg-images

ቼ ጉቬራ

ቼ የመረጠውን መንገድ የመረጡ የትግል ሥልቱን የተከተሉ 
"ፋ ኖ ተሰማራ
ፋ ኖ ተሰማራ 
እንደ ሆ ቺ ሚኒ እንደ ቼ ጉቬራ" 
ሲሉ ይዘምሩለት ነበር። የዛሬን አያድርገው እና።  ቼ ሲሞት የኩባ አብዮት ጀግና እና ምልክት ሆኖ ነበር። የእምቢ ባይነት እና ነፃነትን የመሻት ምልክት ተደርጎም ይቆጠራል። ቼ ግን የሚወቀስባቸው፤ የሚኮነንባቸው ጨለምተኛ ታሪኮችም አሉት። ዘመን ሲያልፍ የትጥቅ ትግል አዋጪነት ቢያጠራጥርም ቼ ግን ጨርሶ አልተዘነጋም። 

ይልማ ኃይለሚካኤል
እሸቴ በቀለ 
ነጋሽ መሐመድ