1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ማርቲን ሹልዝ ሜርክልን ይፎካከራሉ

እሑድ፣ ጥር 21 2009

የጀርመን ሶሻል ዴሞክራቶች ፓርቲ በመጪው መስከረም ለሚካሔደው ብሔራዊ ምርጫ የቀድሞው የአውሮጳ ኅብረት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ማርቲን ሹልዝን እጩነት አጸደቀ።

https://p.dw.com/p/2Wb30
Martin Schulz
ምስል Reuters/H. Hanschke

የጀርመን ዜና አገልግሎት እና ሬውተርስ የዜና ወኪል ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ጠቅሰው እንደዘገቡት በመጪው መጋቢት ፓርቲው ማርቲን ሹልዝን በይፋ ያቀርባል። የ61 አመቱ ማርቲን ሹልዝ ለጀርመን መራሔ-መንግሥትነት አንጌላ ሜርክልን እንዲወዳደሩ 35ቱ የሶሻል ዴሞክራት ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት በሙሉ ድምጽ ዛሬ ማጽደቃቸውን ሬውተርስ ዘግቧል። ማርቲን ሹልዝ ከ20 አመት በላይ በአውሮጳ ምክር ቤት አባልነት አገልግለዋል። ዛሬ በበርሊን የፓርቲው ዋና ፅ/ቤት ንግግር ያደረጉት ሹልዝ በጀርመን ተፈጥሯል ያሉትን «ጥልቅ መከፋፈል» እታገላለሁ ብለዋል። ከ1000 በላይ ለሚሆኑት ታዳሚዎች ፍትኃዊ የግብር ህግጋት እንደሚሰሩም ሹልዝ ተናግረዋል። 

እሸቴ በቀለ

ልደት አበበ