1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሀይማኖታዊ ሳንሱር

ዓርብ፣ የካቲት 6 2001

በጥንታዊ የእስልምና ስነ ፅሁፍ የእስልምና ታሪኮች ውስጥ የሚገኙ ጭብጦችና ገፀ ባህሪያትን አስመልክቶ፤ ነብዩን ጨምሮ በምፀት መጻፍ የተለመደ ጥበብ ነው። በዛሬ ዘመን ስነ ፅሁፍ ግን ሀይማኖታዊ ጉዳዮች ወደጎን ሲደረጉ ይስተዋላል። አለበለዚያ ያለመረዳትና ወደ ሀይል የሚያመራ ድርጊት በተደጋጋሚ ሲከሰቱ ይታያል።

https://p.dw.com/p/Gtgk
ሳልማን ሩሽዲ-ኒውዮርክ
ሳልማን ሩሽዲ-ኒውዮርክምስል AP
የኢራን አብዮት መሪ አያቶላህ ሆሚኒ ከሀያ ዓመታት በፊት የ “The Satanic verses” ሠይጣናዊ ጥቅሶች መጸሀፍ ደራሲና የመጸሀፉ አሳታሚ በሞት እንዲቀጡ ትዕዛዝ ማስተላለፋቸው ይታወቃል። መጸሀፉ የፈጣሪን እና የነብዩን ስም ስለሚያጎድፍም ማንኛውም ሙስሊም ይህን የሞት ትዕዛዝ በደራሲው ላይ እንዲተገብር አያቶላህ ሆሚኒ ውሳኔ አስተላልፈዋል። ከአረብ የእስልምና ዓለም የተገኙት ፈላስፋ ሳዲቅ አል አዚም አሁን አደገኛ ሁናቴ ውስጥ ሊከታቸው በሚችል መልኩ ለደራሲ ሳልማን ሩሽዲና ለመጸሀፉ መከራከር ይዘዋል።