1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሁለተኛው የዓለም ጦርነት የተጀመረበት ሰባኛ ዓመት

ማክሰኞ፣ ነሐሴ 26 2001

በአንፃሩ ከጦርነቱ በኃላ ከአስራ ሁለት ሚሊዮን በላይ ጀርመናውያን ከፖላንድ መባረራቸው ኢፍትሀዊ እንደነበር ከዚሁ ጋር ግንዛቤ ሊሰጠው እንደሚገባም ሜርክል አሳስበዋል

https://p.dw.com/p/JNEV
ዉጊያዉምስል AP

ጀርመን ፖላንድን በመውረር ሁለተኛውን የዓለም ጦርነት የጫረችበት ዕለት ሰባኛ ዓመት ከትናንት ምሽት አንስቶ ፓላንድ ውስጥ በልዩ ልዩ ስነ ስርዓቶች እየታሰበ ነው ። የጀርመንዋ መራሂተ መንግስት አንጌላ ሜርክልና የሩስያው ጠቅላይ ሚኒስትር ቭላድሚር ፑቲን በተገኙበት ሰሜናዊ ፖላንድ ውስጥ በዛሬው ዕለት ዕለቱ የሚታሰብበት ስነ ስርዓት ይካሄዳል ። መራሂተ መንግስት አንጌላ ሜርክል በስነ ስርዓቱ ላይ ለመገኘት ወደ ፓላንድ ከመሄዳቸው በፊት በሰጡት መግለጫ ጀርመን ስልሳ ሚሊዮን ህዝብ ያለቀበትን ሁለተኛውን የዓለም ጦርነት በመጀመር የዓለም ህዝብ ለደረሰበት ሰቆቃ ምክንያት እንደሆነች አስታውሰዋል ። በአንፃሩ ከጦርነቱ በኃላ ከአስራ ሁለት ሚሊዮን በላይ ጀርመናውያን ከፖላንድ መባረራቸው ኢፍትሀዊ እንደነበር ከዚሁ ጋር ግንዛቤ ሊሰጠው እንደሚገባም ሜርክል አሳስበዋል ። ይልማ ኃይለ ሚካኤል

Yilma Hinz ,HIrut Melesse

Negash Mohammed