ሁለተኛ አብዮት በሊቢያ
ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 4 2004ማስታወቂያ
የሰሜን አትላንቲክ የጋራ መከላከያ ቃል ኪዳን ድርጅት ኔቶም ከሊቢያ ወጥቷል ። የሽግግሩ ምክር ቤትም ስልጣኑን ለሽግግር መንግሥቱ አስረክቧል ። ይሁንና የሊቢያ ወጣት አብዮተኞች ፍፁም አልረኩም ። በአሁኑ ጊዜ በ 10 ሺህዎች የሚቆጠሩ ብሔራዊ የሽግግር ምክር ቤቱንና ሊቀ መንበሩን ሙስጠፋ አብደል ጃሊልን በመቃወም ሰልፍ ያካሂዳሉ ። ሌላ አዲስ አብዮት እንዲካሄድ ጥሪ እያስተላለፉ ነው ። የዶቼቬለዋ ሞኒካ ዲትሪሽ የዘገበችውን ሂሩት መለሰ አጠናቅራዋለች ።
ሂሩት መለሰ
አርያም ተክሌ