1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሁለት ፖለቲከኞች ወደአንድነት ፓርቲ ገቡ

ሐሙስ፣ ኅዳር 17 2002

የቀድሞ የኢፌዴሪ ፕሬዝደንት ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ እና የቀድሞ የመከላከያ ሚኒስትር አቶ ስዬ አብረሃ ዛሬ የአንድነት ለፍትህና ለዴሞክራሲ ፓርቲ አባላት ሆኑ።

https://p.dw.com/p/Kh7g
ምስል AP Graphics/DW Fotomontage

ሁለቱም ፖለቲከኞች ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ የሚመሩት አንድነት ፓርቲ አባላት መሆንን የመረጡት አብዛኛዉ እድሜያቸዉን ያሳለፉበት የብሄር ብሄረሰብ ፖለቲካ ለኢትዮጵያ ችግር መፍትሄ አይሆንም በሚል ነዉ። በተለይ ዶክተር ነጋሶ የህገ መንግስቱ አርቃቂ ኮሚሽን ፕሬዝደንት በነበሩበት ወቅት ፈፅሜያለሁ ላሉት ስህተት የኢትዮጵያን ህዝብ በይፋ ይቅርታ ጠይቀዋል።

ታደሰ እንግዳዉ /ሸዋዬ ለገሠ/ነጋሽ መሐመድ