1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሁከት በናይጀሪያ

ረቡዕ፣ ሚያዝያ 12 2003

ባለፈው ቅዳሜ በናይጀሪያ የተካሄደው ፕሬዚደንታዊ ምርጫ ውጤት በሀገሪቱ አሳሳቢ ሁከት አስከተለ። በምርጫው ጉድላክ ጆናታን 57% ከመቶ የመራጭ የድምፅ በማግኘት ተፎካካሪያቸውን ሙሐመድ ቡሐሪን አሸንፈዋል።

https://p.dw.com/p/RJ2n
ፕሬዚደንት ጉድላክ ጆናታንምስል AP

ቡሀሪ 31% ከመቶ የመራጭ ድምፅ ብቻ ነው ያገኙት። የምርጫው ውጤት ይፋ ከሆነ በኋላ ውጤቱን መቀበል ያልፈለጉ የቡሀሪ ደጋፊዎች በተለያዩ ከተሞች ባካሄዱት ሁከት ብዙ ሰዎች ሳይሞቱ እንዳልቀሩ የቀይ መስቀል ማህበር ትናንት አስታውቋል። ሰው ከቦታ ወደ ቦታ እንዳይንቀሳቀስ የሚል አዋጅ ከወጣ በኋላ፤ ለጊዜው ግጭቱ ጋብ ብሏል። በሌላ በኩል የናይጄሪያ ምርጫ የሃይማኖት ልዩነት ማንፀባረቂያ ሆኖም ታይቷል።

ልደት አበበ

ነጋሽ መሐመድ