1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ህዝባዊ ተቃውሞ በቱርክ

ሰኞ፣ ግንቦት 26 2005

በቱርክ ዐብይ ከተማና የንግድ ማዕከል በኢስታንቡል በመቶ ሽህ የሚቆጠሩ ተቃዋሚ ሰልፈኞች ጠቅላይ ሚኒስትር ረችብ ታይብ ኤርዶጋን ስልጣን እንዲለቁ ጠየቁ። ባለፈዉ ሳምንት መጠናቀቅያ ላይ በቱርክ የታየዉ የተቃዉሞ ሰልፍ ከአስር አመት ወዲህ የመጀመርያዉ እንደሆንም ተነግሮአል።

https://p.dw.com/p/18j3n
epa03727991 Protesters are seen in a street during a rally supporting the Istanbul demonstrations against the conservative government of Prime Minister Recep Tayyip Erdogan, in Ankara, Turkey, 02 June 2013. A police crackdown on 31 May in Istanbul against a peaceful sit-in staged by protesters angered over a development project in Istanbul escalated into larger battles between law enforcement and demonstrators, who criticized heavy-handed police tactics. Protesters accuse Prime Minister Erdogan and his Justice and Development Party (AKP) of gradually instituting authoritarian Islamist rule in fiercely secular Turkey and are calling on him to step down. EPA/EVRIM AYDIN/ANADOLU AGENCY TURKEY OUT EDITORIAL USE ONLY/NO SALES/NO ARCHIVES
ምስል picture-alliance/dpa

በቱርክ መዲና አንካራ ፖሊስ ሰልፈኞችን ለመበተን አስለቃሽ ጢስ ተጠቅሞአል። የአዉሮጳዉ ህብረት ፖሊስ በተቃዋሚ ሰልፈኞች ላይ የወሰደዉን እርምጃ አዉግዞአል፤  

በኢስታንቡል ቱርክ በሚገኝ የመዝናኛ ፓርክ ዉስጥ ለቀናቶች የሰፈሩ የተቃዎሞ ሰልፈኞችን በሳምንቱ መጠናቀቅያ የጸጥታ ፖሊስ  ለመበተን ባደረገዉ ጥረት በርካቶች የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸዉ ተነግሮአል። በኢስታንቡል «ጌዚ» የተሰኘዉ የመዝናኛ ፓርክ ፈርሶ የንግድ ማዕከል ግንባታ ስራ እንዲካሄድ  መንግስስት የወጣዉን ትእዛዝ በመቃወም በርካታ ተቃዋሚዎች፤ ለቀናቶች ማደርያ መዋያቸዉን ፓርክ ዉስጥ በማድረጋቸዉ፤ ጠቅላይ ሚንስትር ራችብ ኦርዶጋን ተቃዋሚዎች በሃይል ከቦታዉ እንዲነሱ በማዘዛቸዉ ነበር ባለፈዉ ሳምንት አርብ ምሽት በተቃዋሚዎች እና በፀጥታ አስከባሪዎች መካከል የተነሳዉ ግጭት የጠነከረዉ። ፖሊስ በፓርኩ የሰፈሩትን ተቃዋሚ ሰልፈኞች ከቦታዉ ለማስነሳት ዉሃ በመርጨት እና  አስለቃሽ ጋዝን ተጠቅሞአል። አርብ ምሽት የቀተቀሰቀሰዉ ግጭት ቅዳሜ ዕለትም  በኢስታንቡል ታክዚም በሚባል አደባባይ እና ጌዚ የመዝናኛ ፓርክ አቅራብያ በፖሊስ እና በተቃዋሚ ሰልፈኞች መካከል ቀጥሎ ነበር የዋለዉ፤ ተቃዋሚ ሰልፈኞቹ፤ የመዝናኛ ፓርኩ እንዳይፈርስ ብሎም፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ራችብ ኤርዶጋን ስልጣን እንዲለቁ ይጠይቃሉ።  አንድ የኢስታንቡል ነዋሪ እንደተናገሩት

Tear gas surrounds a protestor holding a Turkish flag with a portrait of the founder of modern Turkey Mustafa Kemal Ataturk as he takes part in a demonstration in support of protests in Istanbul and against the Turkish Prime Minister and his ruling Justice and Development Party (AKP), in Ankara, on June 1, 2013. Turkish police on June 1 began pulling out of Istanbul's iconic Taksim Square, after a second day of violent clashes between protesters and police over a controversial development project. Thousands of demonstrators flooded the site as police lifted the barricades around the park and began withdrawing from the square. What started as an outcry against a local development project has snowballed into widespread anger against what critics say is the government's increasingly conservative and authoritarian agenda. AFP PHOTO / ADEM ALTAN (Photo credit should read ADEM ALTAN/AFP/Getty Images)
ምስል Adem Altan/AFP/Getty Images

«ፖሊስ እጅግ ከፍተኛ የሆነ ጥቃት ነዉ የጣለዉ፤ በእዉነቱ ከሚገባዉ በላይ የሆነ ጥቃት ነዉ። በእንደዚህ አይነቱ ሁኔታ ፖሊስ ህዝቡን በጠበቅ እና መከላከል ነበር የነበረበት»

ጠቅላይ ሚኒስትር ኤርዶጋን የፀጥታ አስከባሪዎች በተቃዋሚ ሰልፈኞች ላይ ያደረሱትን ጥቃት ስህተት መሆኑን ቢቀበሉም፤ ተቃዋሚ ሰልፈኞቹ ስርዓት አልባ የሆኑ  የዲሞክራሲ ጠላቶች ናቸዉ ሲሉ ኮንነዋል።

«ተቃዋሚ ሰልፈኞቹ መሪት ላይ የተነጠፈዉን  የተጠረበ ድንጋይ ፈነቃቅለዉ የሱቅ መስኮቶች ላይ ወርዉረዋል። እና ይህ ዴሞክራሲ ነዉ? ራችብ ታይብ ኤርዶጋን አንባገነን ነዉ ብለዋል። ለህዝቡ ምቾት የሚሰራዉን ሰዉ ነዉ፤ አንባገነን  ብለዉ ከጠሩ የምለዉ ነገር አይኖርም»

በኢስታንቡል በሚገኘዉ የመዝናኛ ፓርክ፤ ትናንት እሁድ፤ ከብጥብጥ ይልቅ ሰላም ነግዞ ነዉ የዋለዉ። በሺዎች የሚቆጠሩ ሰልፈኞች፤ በመዝናኛ ፓርኩ የሚበላ የሚጠጣ በማምጣትና ሙዚቃን በመክፈት ባለፉት ቀናት የነበረዉን ሃይል የቀላቀለ ብጥብጥ እና የተቃዉሞ ሰልፍ ፊቱን እንዲቀይር ለማድረግ ሞክረዋል። በመዝናኛ ፓርኩ አቅራብያ ያለዉ ክፈለ ከተማ ነዋሪዎች ጌዚ ፓርክ ተነስቶ ለንግድ ማዕከል የሚሆን ግንባታ ስራ እንዳይደረግ ትግላቸዉን ቀጥለዋል። ይኸዉም ታኪዚም አደባባይ ላይ መንገድን በአትክልት፤ በአግዳሚ ወንበር እና በአዉቶቡስ በመከለል ፖሊስ ወደ ስፍራዉ እንዳይገባ ከልለዋል። በኢስታንቡል መሃል ከተማ የህዝቡ ቁጣ እንዳየለ ነዉ። በኢስታንቡል በተቃዋሚ ሰልፈኞች እና ፖሊስ መካከል የደረሰዉን ብጥብጥ ተከትሎ በቱርክ ትላልቅ ከተሞች ማለት አንካራ እና ኢዝሚር በተቃዋሚዎች እና በጸጥታ አስከባሪ ፖሊሶች መካከል ብጥብጥ መቀስቀሱም ተነግሮአል። በፖሊስ እና በተቃዋሚ ሰልፈኞች መካከል በደረሰዉ ዉጥረት በተከሰተዉ አደጋ እስካሁን የስምንት ሚሊዮን ይሮ ንብረት መዉደሙን የቱርክ የአገር ዉስጥ ሚኒስትር ሙአመር ጉሊየር ይፋ ተናግረዋል።

A demonstrator sits on the ground after he was detained by riot police during an anti-government protest in Izmir, western Turkey, June 2, 2013. Protesters lit fires and scuffled with police in parts of Istanbul and Ankara early on Sunday, but the streets were generally quieter after two days of Turkey's fiercest anti-government demonstrations for years. Interior Minister Muammer Guler said on Saturday that 939 people had been arrested in more than 90 separate demonstrations around the country. REUTERS/Emre Tazegul (TURKEY - Tags: POLITICS CIVIL UNREST)
ምስል picture-alliance/dpa

በሌላ በኩል በብጥብጡ የደረሰዉን የንብረት መጥፋት ምክንያት በማየት የተቃዋሚ ወገኖች የሚቃወሙ የኢስታንቡል ነዋሪዎችም አሉ፤

«አላስፈላጊ የሆነ የተቃዎሞ ሰልፍ ነዉ። አንድ ሰዉ የማይፈልገዉን ነገር ለማሳየት ወይም ለመናገር ከፈለገ ሌላ ሌላ ፍላጎትን የሚገልጽበት ዘዴ አለ። እኔ እንደሚመስለኝ እዚህ የታየዉ ሁሉ ትክክለኛ ነገር አይደለም »   

የቱርኩን ጠቅላይ ሚኒስትር ራችብ ኤርዶጋንን በመቃወም በቱርክ በተለያዩ ከተሞች የተቃዎሞ ሰልፍ  ቢቀሰቀስም ጠቅላይ ሚኒስትር ራችብ ኤርዶጋንን  ዉጭ ሃገራትን  ለመጎብኘት ቀደም ሲል የያዙትን ቀጠሮ ጀምረዋል። ኤርዶጋን ከሚጎበኝዋቸዉ አገሮች መካከል ሞሮኮ እና አልጀርያ ሲገኙበት ጉብኝታቸዉን የፊታችን ሃሙስ አጠናቀዉ ወደ አገራቸዉ እንደሚመለሱ ይጠበቃል።  

አዜብ ታደሰ

ተክሌ የኋላ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ