ለሕጻናት በቂ የተመጣጠነ ምግብ UNICEF
ሐሙስ፣ ኅዳር 16 2008ማስታወቂያ
በአሁኑ ጊዜ ድርቁ እየከፋ በመሄዱ የተባበሩት መንግሥታት የተለያዩ ድርጅቶች ለድርቅ ተጎጂዎች ተገቢዉ ርዳታ እንዲደርስ የየበኩላቸዉን ግዳጅ ለመወጣት እየሠሩ እንደሚገኙ የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ጌታቸዉ ተድላ ኃይለጊዮርጊስ በላከዉ ዘገባ ጠቅሷል። ድርጅቶቹ በተቀናጀ መንገድ በቅርቡ በጋራ ጉዳዩን አስመልክተዉ የጋዜጣዊ መግለጫ እንደሚሰጡ ይጠበቃል። እንዲያም ሆኖ የተባበሩት መንግሥታት የሕፃናት አድን ድርጅት በእንግሊዝኛ ምህፃሩ UNICEF በየትኛዉ ስፍራ ድርቅ ሲከሰት ፈጥነዉ ለጉዳት ለሚዳረጉት ሕጻናት በቂ የተመጣጠነ ምግብ አቅርቦት እንዳለዉ አመልክቷል። ጌታቸዉ የድርጅቱን ኃላፊ በማነጋገር ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል።
ጌታቸዉ ተድላ ኃይለጊዮርጊስ
ሸዋዬ ለገሠ
አርያም ተክሌ