1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

“ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፖሊስ ተይዘው ይቅረቡ”- አቶ በቀለ ገርባ

ማክሰኞ፣ ታኅሣሥ 17 2010

በኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ምክትል ሊቀመንበር አቶ በቀለ ገርባ በመከላከያ ምስክርነት ለዛሬ የተጠሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ቀሩ፡፡ አቶ በቀለ “ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፖሊስ ተይዘው ሊቀርቡ ይገባል” ብለዋል፡፡

https://p.dw.com/p/2pxzp
Äthiopien Journalisten Martin Schibbye und Johan Persson
ምስል AP

“ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፖሊስ ተይዘው ሊቀርቡ ይገባል”- አቶ በቀለ ገርባ

በእስር ላይ ባሉበት “ጤንነታቸው መቃወሱን እና ህክምናም አለማግኘታቸው” የተነገረላቸው የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ምክትል ሊቀመንበር አቶ በቀለ ገርባ ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርበው ነበር፡፡ አቶ በቀለ ዛሬ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራተኛ ወንጀል ችሎት የተገኙት በመከላከያ ምስክርነት የቆጠሯቸውን ግለሰቦች የምስክርነት ቃል ለማስደመጥ ነበር፡፡ 

መከላከያ ምስክርነት ከተጠሩት ውስጥ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ እና የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ለማ መገርሳን ጨምሮ አምስት የመንግስት ኃላፊዎች ይገኙበታል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስክርነት መጥሪያ ቢደርሳቸውም ዛሬ በችሎት አልቀረቡም፡፡ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽህፈት ቤት ለፍርድ ቤቱ በላከው ደብዳቤ “በስራ መደራረብ ምክንያት ሊቀርቡ አይችሉም” ብሏል፡፡ አቶ በቀለ እና ጠበቃቸው ይህንኑ ተቃውመዋል፡፡ የዛሬውን የችሎት ውሎ የተከታተለዉ ዮሃንስ ገብረእግዚያብሔር ከአዲስ አበባ የላከውን ዘገባ የድምጽ ማዕቀፉን በመጫን ያድምጡ፡፡  

ዮሃንስ ገብረእግዚያብሔር

ነጋሽ መሐመድ