1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ለሶማሊያ የሠላም መፍትሄ ከአፍሪቃ ህብረት

ቅዳሜ፣ መጋቢት 19 2001

ሶማሊያን በተመለከተ ሰሞኑን የአፍሪቃ ህብረት የፀጥታው ምክር ቤት ተከታታይ ስብሰባዎችን አካሂዶ ነበር። ውይይቱ በውትድርናው መስክ አንዳንድ አባል ሀገራት ቃል በገቡት መሰረት የሠላም አስከባሪ ሠራዊት በተጨማሪ የሚልኩበትን ሁኔታና፤ በተጓዳኝ በሀገሪቷ ፖለቲካዊ መፍትሄ ማፈላለጉ ላይ ያተኮረ ነበር።

https://p.dw.com/p/HLpR
የሶማሊያ ተስፋ
የሶማሊያ ተስፋምስል AP

በጎረቤት ሶማሊያ ለአስራ ስምንት ዓመታት የዘለቀው የርስ በርስ ጦርነት ይህ ነው የተባለ መቋጫ እስካሁን ባለማግኘቱ ብዙዎችን አሳስቧል። ይህ በመሆኑም የአፍሪቃ ህብረት የፀጥታው ምክር ቤት በተደጋጋሚ ባደረገው ስብሰባ አባል ሀገራት የገቡትን ቃል እንዲያከብሩ ጠይቋል። የአፍሪቃ ህብረት የሠላም አስከባሪ ሀይል፤ በተባበሩት መንግስታት እስኪተካ ድረስ እንደሚሰራም ተገልፃል። ይህ በእንዲህ እንዳለም ኡጋንዳ ተጨማሪ የሠላም አስከባሪ ወታደሮችን መላኳ ታውቋል።

ጌታቸው ተድላ

ማንተጋፍቶት ስለሺ