1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ለብቻቸዉ የሚሰደዱ ሕጻናት መበርከት

ሐሙስ፣ ግንቦት 17 2009

የተባበሩት መንግሥታት የሕጻናት መርጃ (UNICEF) ለብቻቸው የሚሰደዱ ሕጻናት ቁጥር በአምስት እጥፍ ማደጉን በሪፖርቱ አስታወቀ፡፡ ድርጅቱ ባወጣው ዘገባ ከጎርጎሪዮሳዊዉ 2010 ወዲህ ያለ አጃቢ ለብቻቸው የሚሰደዱ ሕጻናት ቁጥር ከዚህ ቀደም ባልታየና በአስደንጋጭ መልኩ ማደጉን ነው የገለጸው፡፡

https://p.dw.com/p/2dZet
Mittelmeer Mehr als 6000 Bootsflüchtlinge gerettet
ምስል picture alliance/Pacific Press/A. Di Vincenzo

M M T/ Beri. Toronoto (UNICEF report unaccompanied children) - MP3-Stereo

እንደ ዘገባዉ ከሆነ በ2015 እና 2016 ብቻ ቢያንስ 300 ሺህ ሕጻናት ከ80 የተለያዩ ሃገራት ተሰደው የወጡ ሲሆን፣ ይህ አሀዝ በ2010 እና 2011 ከተመዘገበው 66 ሺህ አጃቢ የለሽ ሕጻናት ስደተኞች ቁጥር ጋር ሲነጻጸር በአምስት እጥፍ ጨመሮ ታይቷል፡፡ ዩኒሴፍ የፊታችን ዓርብ በሚጀምረው የ7ቱ የበለጸጉ ሃገራት ጉባኤ ላይ ጉዳዩ ትኩርት እንዲሰጠው ተማጽኗል፡፡  ዘጋቢያችን አክመል ነጋሽ ከቶሮንቶ ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።

አክመል ነጋሽ

ሸዋዬ ለገሠ

አርያም ተክሌ