1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ለኔልሰን ማንዴላ መታሰቢያ በአፍሪቃ ኅብረት አዳራሽ

እሑድ፣ ኅዳር 29 2006

የደቡብ አፍሪቃ ብሔራዊ ኮንግረስ ታዋቂ አባልና በተጨማሪ የትጥቁ ትግል ክንፍ፣ «የህዝብ ጦር » (Umkhonto we Sizwe)የተሰኘው ኀይል መሪ የነበሩት፤ 27 ዓመታት በእሥራት የማቀቁትና ዘረኛውን ሥርዓት አፓርታይድን ድል አድርገው ፣ በዴሞክራሲ ለመመረጥ

https://p.dw.com/p/1AVfQ
Trauer um Nelson Mandela
ምስል Reuters

የመጀመሪያው የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ለመሆን የበቁትና የኖቤል የሰላም ተሸላሚ ፤ ኔልሰን ማንዴላ፤ ባለፈው ሐሙስ ማታ ካረፉ ወዲህ፤ አዲስ አበባ ውስጥ በአፍሪቃ ኅብረት አዳራሽ በልዩ ሥነ ሥርዓት ዝካሬ ተደርጎላቸዋል። በዚህ ልዩ ሥነ ሥርዓት ፣ በአዲስ አበባ ከሚኖሩት አምባሳደሮችና የተለያዩ የሃይማኖት መሪዎች ጋር ፣ የኅብረቱ ዋና ጸሐፊ ወ/ሮ ድላሚኒ ዙማና በዙር ምርጫ መሠረት የዘንድሮው የአፍሪቃ ኅብረት ፕሬዚዳንት አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ተገኝተዋል።

ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ

ተክሌ የኋላ

ነጋሽ መሐመድ