1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ለአዲስ አመት የእንኳን አደረሳችሁ መልክት

ቅዳሜ፣ ታኅሣሥ 21 2004

የጀርመንዋ መራሂተ መንግስት አንጌላ ሜርክል ለህዝባቸዉ እንኳን ለአዲሱ የጎርጎረሳዉያን 2012 አ.ም አደረሳቸዉ መልክት አስተላለፉ።

https://p.dw.com/p/13cMK
ምስል Picture-Alliance/dpa

በአዉሮጳ በዩሮ ተጠቃሚ አገሮች የየዕዳ ቀውስ ቢከሰትም ህብረተሰቡ በህብረት መቆም እንደሚገባዉ የጀርመኗ መራሂተ መንግስት አንጌላ ሜርክል አስታወቁ። ሜርክል ይህን ያሉት ዛሪ የሚብተዉን አዲሱን የጎርግረሳዉያን 2012 አመተ-ምህረት በማስመልክት የእንኳን አደረሳችሁ መልክት ባስተላለፉበት ወቅት ነዉ። መራሂተ መንግስቷ ማህበረሰቡ በአዉሮጻ ህብረት እና በጋራ ሸርፉ ይሮ ላይ እምነቱን እንዲጥልም ጠይቀዋል። የዛሪ አስር አመት በአዉሮጻ ህብረት አባል አገራት ብቅ ያለዉ የጋራ መጠቀምያ ሸርፍ ይሮ በአገራቱ መካከል ያለዉን ግንኙነት እና ሁኔታ አቅልሎታል የምጣኔ ሃብቱን ሁኔታም እጅግ አጠናክሮታል ብለዋል። በሸርፉ አገራት የተከሰተዉን የእዕዳ ቀዉስ በመንተራስ ሜርክል የጋራ ሸርፉን ጠንካራ ለማድረግ የተቻላቸዉን ሁሉ እንደሚያደርጉም ገልጸዋል። መራሂተ መንግስቷ ከዕዳ ቀዉሱ ለመዉጣት ገና ረጅም እና ከባድ ጉዞን እንደሚጠይቅ አስታዉሰዉ አዉሮጳ ከችግሩ በጥንካሪ እንደሚወጣ ያላቸዉን እምነት ገልጸዋል። በሌላ በኩል ሜርክል በጀርመን ከቅርብ ሳምንታቶች ወዲህ ይፋ የወጣዉ አንድ የቀኝ አክራሪዎች ቡድን ያደረገዉን የግድያ ወንጀል በማሰብም ህዝባቸዉ በጥሞና እና በመተሳሰብ በጋራ እንዲቆም ጥሪ አቅርበዋል።

አዜብ ታደሰ
ልደት አበበ