1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ግጭቱ ከመሬት ይገባኛል ጋር የተያያዘ ነው ተብሏል

ዓርብ፣ ታኅሣሥ 13 2010

በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን እና በደቡብ ክልል አማሮ ወረዳ የኮሬ ማኅብረሰብ ነዋሪዎች መካከል ባለፈው አመት ሰኔ ወር የተቀሰቀሰው ግጭት ጋብ ያለ ቢመስልም አሁንም መቀጠሉን ከአካባቢው የተገኘ መረጃ ይጠቁማል። ግጭቱ ከመሬት ይገባኛል ጋር የተያያዘ እንደሆነ የአካባቢው ባለስልጣን እና የተቃዋሚ አባል ገልጸዋል።

https://p.dw.com/p/2prHh
12.06.2013 DW Online Karten Basis Äthiopien Englisch

ግጭቱ ከመሬት ይገባኛል ጋር የተያያዘ ነው ተብሏል

በደቡብ ክልል የሚገኙ የሶሻል ዲሞክራቲክ ፓርቲ አባል ለዶይቼ ቬሌ እንደተናገሩት  ከትላንት በስቲያ ምሽት ረቡዕ ጭምር ግጭት ነበር። በዚህም ሰዎች መሞታቸውን ተናግረዋል። የአማሮ ወረዳ አስተዳዳሪ በበኩላቸው ከመሬት ይገባኛል ጋር በተያያዘ ግጭት እንደነበር ያምናሉ። ሁኔታው እየተረጋጋ እንደሆነ ቢገልጹም ዘላቂ ሰላም ተፈጥሯል ብሎ መናገር እንደማይቻል አመልክተዋል። የአዲስ አበባው ወኪላችን ጌታቸው ተድላ ኃይለጊዮርጊስ ሁለቱንም ወገኖች አነጋግሯል። ዝርዝር ዘገባውን የድምጽ ማዕቀፉን በመጫን ያድምጡ።

ጌታቸው ተድላ ኃይለጊዮርጊስ

ሸዋዬ ለገሠ