1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ለደቡብ ሱዳኑ ረሀብ የአውሮጳ ህብረት እርዳታ 

ረቡዕ፣ የካቲት 15 2009

የኮሚሽኑ ቃል አቀባይ ለዶቼቬለ እንደተናገሩት ኮሚሽኑ ለረሀብ አደጋው መርጃ ተጨማሪ 82 ሚሊዮን ዩሮ ይለግሳል ።

https://p.dw.com/p/2Y4sn
Südsudan Mehr als 30.000 Menschen laut UNO vom Hungertod bedroht
ምስል Getty Images/AFP/T. Karumba

Beri Brussels (Südsudan-Hunger-EU Hilfe) - MP3-Stereo

ለጋሾች ለደቡብ ሱዳኑ የረሀብ አደጋ መርጃ የሚውል እርዳታ እየሰጡ እና ቃል እየገቡም ነው ። ከመካከላቸው አንዱ የአውሮጳ ህብረት ኮሚሽን ነው ። ኮሚሽኑ ለደቡብ ሱዳኑ ረሀብ መቋቋሚያ የሚውል ተጨማሪ እርዳታ እንደሚሰጥ አስታወቋል ። የኮሚሽኑ ቃል አቀባይ ለዶቼቬለ እንደተናገሩት ኮሚሽኑ ለረሀብ አደጋው መርጃ ተጨማሪ 82 ሚሊዮን ዩሮ ይለግሳል ። የተባበሩት መንግሥታት የህጻናት መርጃ ድርጅት በምህፃሩ UNICEF እንደሚለው በሱዳኑ ረሀብ ለሞት አደጋ ከተጋለጡት መካከል በርካታ ህጻናት ይገኙበታል ።

ገበያው ንጉሴ

ሂሩት መለሰ