1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ለደቡብ ሱዳንን የተሰጠው ማስጠንቀቂያ

ሐሙስ፣ መጋቢት 11 2006

የአውሮፓ ሕብረትና ዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ፤ በምሥራቅ አፍሪቃ የልማት በይነ መንግሥታት (ኢጋድ) የሚመራውን የደቡብ ሱዳን የሰላም ድርድር በሚያደናቅፉት ላይ ጠንካራ እርምጃ እንደሚወስዱ አስጠነቀቁ። የሕብረቱና የአሜሪካ ተወካዮች፤ አምባሳደር ዶናልድ

https://p.dw.com/p/1BTRK
ምስል Reuters

ቡትዝና አሌክስ ሮንዶስ፤ ትናንት ማምሻውን ለውጭ ሃገራት ጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ላይ እንዳስታወቁት፤ ማስጠንቀቂያቸው ለሁሉ ቢሆንም፤ ይበልጥ በመንግሥት ላይ ያነጣጠረ ነው ተብሏል። ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ ይካሄዳል ተብሎ የተጠበቀው የሰላም ውይይት 7 የቀድሞ የተቃዋሚ ወገን መሪዎች በውይይቱ እንዲካፈሉ ከአማፅያን በኩል የቀረበው ጥያቄ በጁባ መንግስት ተቀባይነት ባለማግኘቱ ሳይከናወን ቀርቷል። ሁለቱ ወገኖች በአሁኑ የሰላም ንግግር አንድ ውጤት ላይ ካልደረሱና በተፈራረሙት የተኩስ አቁም ስምምነት ካልፀኑ የማዕቀብ ቅጣት ሊጠብቃቸው እንደሚችል የአውሮፓ ህብረትና ዩናይትድ ስቴትስ ትናንት አስጠንቅቀው ነበር ። በደቡብ ሱዳን የአውሮፓ ህብረት ልዑክ አሌክሳንደር ሮንዶስ ትናንት አዲስ አበባ ውስጥ እንደተናገሩት የአውሮፓ ህብረት የፖለቲካ ሂደቱን በሚያደናቅፉ ግለሰቦች ላይ ያነጣጠሩ እርምጃዎችን ከግምት ውስጥ ለማስገባት ተዘጋጅቷል ።የዩናይትድ ስቴትሱ አቻቸው ዶናልድ ቡዝም ዋሽንግተን የሚወሰዱት እርምጃዎች ምን ሊሆኑ እንደሚችሉ እያሰበች መሆኑን ተናግረዋል

ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር

ተክሌ የኋላ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ