1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ለፋሽስት ጣሊያን ወረራ ግፍ ካሳ መጠየቁ

ሰኞ፣ መስከረም 17 2008

በፋሺስት ጣሊያን ወረራ ወቅት ለተፈፀመዉ ግፍ ካሳ እንዲሰጥ ባሳለፍነዉ ቅዳሜ በዋሽንግተን ዲሲ ዩናይትድ ስቴትስ በተካሄደ ዓለም አቀፍ ጉባኤ ላይ ተጠየቀ።

https://p.dw.com/p/1GerZ
USA Haushaltskrise Shutdown Freiheitsstatue
ምስል picture alliance / empics

ዓለም አቀፍ ሕብረት ለፍትሕ - የኢትዮጵያ ጉዳይ ድርጅት ባካሄደዉ በዚህ ጉባኤ በወረራዉ ወቅት ስለተፈፀመዉ ግፍ እና ቫቲካንን ድጋፍ የዘረዘሩ የጥናት ጽሑፎች መቅረባቸዉን በቦታዉ የተገኘዉ የዋሽንግተኑ ወኪላችን መክብብ ሸዋ በላከዉ ዘገባ ገልጾልናል። በፋሺስት ኢጣልያ ወረራ ወቅት ኢትዮጵያ ላይ የተፈፀመዉ አሰቃቂ የጦር ወንጀል ይቅርታ እንዲጠየቅ ከሃገሪቱ የተዘረፈዉ ንብረት እንዲመለስ በሚል ፍትህን የሚጠይቁ ጽሑፎች በምሑራን አንደበት ተተንትነዋል።


መክብብ ሸዋ
አዜብ ታደሰ
ሸዋዬ ለገሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ