1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ለ HIV AIDS ክትባት ማግኘቱ ምነው አዳገተ

ረቡዕ፣ ኅዳር 20 2004

እንደሚታወቀው፤ ነገ፣ ማለትም እ ጎ አ ታኅሳስ 1 ቀን፤ የተባበሩት መንግሥታት በወሰነው መሠረት፤ ኤች አ ይ ቪ ኤይድስን ለመከላከል ፣ዓለም-አቀፍ መታሰቢያ ዕለት ነው። የመታሰቢያው ዕለት እ ጎ አ ከ 1988 ዓ ም አንስቶ በተለያዩ መርኀ-ግብሮች ይዘከራል።

https://p.dw.com/p/RzUj
ምስል picture-alliance/dpa

እ ጎ አ በ ከ 1980ኛዎቹ ዓመታት አንስቶ ባፋጣኝ መላውን ዓለም ያደረሰው HIV-AIDS ፣ ተኀዋሲው በደፈናው 34 ሚሊዮን ገደማ በሚሆኑ ሰዎች ሰውነት ውስጥ እንደሚገኝ የተረጋገጠ ሲሆን ፤ የመከላከያው እርምጃ በጥሞና ተግባራዊ ካልሆነ፤ መስፋፋቱን ከመቀጠል አንዳች የሚያግደው ሁኔታ አይኖርም።

ፍቱን መከላከያ ሊሆን እንደሚችል በማሰብ ተመራማሪዎች ባለፉት 20 ዓመታት አትኩረው የቆዩበት ጉዳይ ክትባት ፍለጋ ነበር። ግን እስካሁን ፍጹም አስተማማኝ ክትባት ማቅረብ የቻሉ አይመስሉም ። ምክንያቱ ምን ይሆን? ባለፉት 15 ዓመታት ጀርመን ውስጥ በቦኹም ከተማ የሩር አውራጃ ዩኒቨርስቲ፣ ለ «ኤች አይ ቪ ኤይድስ» ክትባት ፍለጋ ሲመራመሩ የቆዩት የተኀዋስያን ጉዳይ ምሁር Klaus Überla እንዲህ ይላሉ።--

1,«አንዱ ዋና ነጥብ፣ «ኤች አይ ቪ» እጅግ ተለዋዋጭ መሆኑ ነው። ይህ ማለት ምንድን ነው? ትግሉ ከአንድ ተኀዋሲ ጋር ብቻ ሳይሆን፤ መሬትን እንደሚያልብስ የክረምት አግቢ መንጋ፤ በሰው አካል ውስጥ ወረራ ከሚያካሂዱ እጅግ ብዛት ካላቸውና ከሚለዋወጡ ተኀዋስያን ጋር በመሆኑ ነው። ስለሆነም ራስን ከብዙ የተለያዩ ኤች አይ ቪዎች መከላከል የሚያስችል ክትባት ለማግኘት እንዳስቸገረ ነው።»

ባልደረቦቻቸው፤ እ ጎ አ በ1984 ፣ ኤች አይ ቪውን ለይተው ለማወቅ መቻላቸውን ካስታወቁ በኋላ፤ የጊዜ ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር፤ ለ ኤች አይ ቪ ክትባት መገኘቱ እንደማይቀር ነበረ ያኔ የተነገረው። ለልጆች ልምሻ(ፖሊዮ)ም ሆነ ለዕብድ ውሻ ልክፍት መላ እንደተገኘ ሁሉ ለዚህም በተመሳሳይ ሁኔታ አብነቱ ይገኝልታል ተብሎ ነበር። ቀደም ሲል ለተጠቀሱት በሽታዎች፤ የከሰመ በሽታ ቀስቃሽ ተኃዋሲን መርፌ በመውጋት ነበረ አብነቱን ማግኘት የተቻለው፤ ይሁን እንጂ፤ ተመራማሪዎቹ ወዲያው ነበረ፣ HIV የተለየ መሆኑን የተገነዘቡት። በሰውነት ውስጥ በተለያዩ ኅዋሳት በተጣመረ ፕሮቲን ውስጥ የሚያግጥም ተኀዋሲ ፣ አንዱ ከሌላው የተለየ ነው። በሌላም በኩል ኤች አይ ቪ፤ በአካል ውስጥ ስለሚደበቅ፤ በሽታን የመከላከያው መዋቅር በሽታ አስተላላፊ አድርጎ ስለማይቆጥረው አይታገለውም።

ታዲያ ይህን የመሰለ ውስብስብ ያለ ሁኔታ መኖሩ እየታወቀ እስፓኝ ውስጥ አንድ ተመራማሪ ቡድን፤ በፈለሰፈው የክትባት መድኃኒት ውጤት ማግኘት የመቻሉ ሁኔታ እንዳጠራጠረ ነው። እስካሁን በተደረገው ምርምር መሠረት ፤ ለኤች አይ ቪ ኤይድስ፣ ገና አስተማማኝ ክትባት አልተገኘለትም። ኤች አይ ቪን ለመከላከል ፣ በተከተቡና ባልተከተቡ ሰዎች መካከል ያለውን ልዩነት ለይቶ ለማሳየት በቤተ ሙከራ ተከናውናል።

//በሙከራው ፣ ክትባት የተደረገላቸው፤ ለጤንነታቸው ልዩ ጥበቃ ሳይደረግ ነው። ቤተ ሙከራ ውስጥ ፣ በከሰመ የኤች አይ ቪ ተኀዋሲ ክትባት ቢደረግም ፤ተኃዋሲውን ወደ ኅዋስ ጥሶ ከመግባት አላስቆመውም።

በመሆኑም ጠበብቱ አዲስ ስልት መቀየስ ነበረባቸው። የተኀዋሲውን ሳይሆን የዘር ባህርይ መለያውን አዘጋጁ፤ ከዚያም ፣ ጎጂነት የሌለው የጉንፋን ተኀዋሲ በመርፌ ጨመሩበት። ፣ የኤች አይ ቪ የዘር መለያው በተከተበው ኅዋሳት እንዲሠርጽ ተደረገ ማለት ነው። የተኃዋሲው ፕሮቲንም በኅዋሳቱ ይሆናል የሚዘጋጀው። በነባቤ ቃል መሠረት፤ የተከታቢው በሽታን የመከላከል ስልትና አቅም፤ ፕሮቲኑን መታገልን ፣ ውሎ አድሮም ትክክለኛውን ጥቅል ተኀዋሲ ወይም ባይረስ መጋፈጥ ነበረበት ማለት ነው። ጠበብቱም ሆኑ ተመራማሪዎቹ፣ ከ «ሜሬክ» የመድኃኒት ፋብሪካ ጋር በመተባበር ለአዎች የሚውል ክትባት ማዘጋጀት የሚቻልበት ዕድል ይኖራል ብለው ሲጠብቁ፤ ምርምራቸው ባስደነጋጭ ሁኔታ ፤ ለሙከራ የተከተቡ ሰዎች ካልተከተቡት በላቀ ሁኔታ በኤች አይ ቪ የመያዝ አደጋ እንደሚያጋጥማቸው ጠቁሞአቸዋል። በመሆኑም ሜሬክ በዚህ ረገድ የሚደረገውን ትብብር አቋርጧል።

ክላውስ ዑዑበርላ፤ ከ 2 ዓመት በፊት በታይላንድ የተደረገው ክሊኒካዊ ምርመራ፤ ጠበብት፤ ኤች አይ ቪ ኤይድስን ከሞላ ጎደል 30 ከመቶ መታገል የሚያስችል ደርሰው እንደነበረ ጠቅሰው ሆኖም ይህ ም ያን ያህል የሚያስፈነድቅ እንዳልነበረ ገልጸዋል። በአሁኑ ጊዜ እንደሚታወቀው፤ ኤች አይ ቪ ኤይድስ፣ የሚተላለፈው፤ ወደ ኅዋሳት በሚዘልቅ በአንድ የተኀዋሲ ጥቃት ነው።

5,«ይህ ማለት እንግዲህ ምንድን ነው፤ አንድ መድኃኒት፤ የበሽታ መጋባትን እስከዚህም ሊከላከል ይችላል ማለት አይደለም። የክትባት መድኃኒት፤ ገሚሱን የተኃዋሲ ሥርጸት ከገታ ፤ 50 ከመቶ የበሽታ መተላለፍን ያግዳል ማለት ነው። »

የተኀዋሲ ተመራማሪ ክላውስ የሆነው ሆኖ ምርምሩ እንደሚቀጥልና ምንም እንኳ ከታሰበው በላይ ረዘም ያለ ጊዜ ቢወስድም፤ ኤች አይ ቪ ኤይድስን ለመከላከል የሚያስችል ክትባት መቅረቡ እንደማይቀር ባለሙሉ ተስፋ ናቸው።

ወደ ቀጣዩ ርእስ እንለፍ። በኢትዮጵያ ለምግብ ጥራት የምሥክር ወረቀት የሚሰጠው ዋና መ/ቤቱ በእስዊትስዘርላንድ የሚገኘው Institute for Market Ecology የተሰኘው ድርጅት ተጠሪ ከሆኑት ዶ/ር አሸናፊ ገዳሙ ጋር ፣ ባለፈው ሳምንት ከጀመርነው ቃለ-ምልልስ በመቀጠል አሁን ሁለተኛውን እናቀርባለን።

ተክሌ የኋላ

ሸዋዬ ለገሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ