1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ለ25ዓመታት የተደጋገመዉ ረሃብ

ሰኞ፣ ነሐሴ 11 2001

በ1977ዓ,ም በኢትዮጵያ ተከስቶ የነበረዉ ረሃብ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ወገኖችን ህይወት ቀጥፏል።

https://p.dw.com/p/JD1O
ምስል DW-TV

በርካቶችም የተወለዱበትና ያደጉበትን ቀዬ እንዲለቁ አስገድዷል። እያሰለሰ ለሚታየዉ ረሃብና ድርቅ ዛሬም አገሪቱ መፍትሄ ማበጀት የቻለች አትመስልም። በሎንዶን ለእይታ የቀረበዉ አንድ ጥናታዊ ፊልም ይህንኑ ሃቅ ያመላክታል። በአንድ ወጣት አርሶ አደር ህይወት ዙሪያ ተመስርቶ እዉነታዉን የፈተሸዉን ጥናታዊ ፊልም በብሪታንያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አብዛኛዉን አርሶ አደር አይወክልም ሲል ተችቷል።

ሃና ደምሴ/ሸዋዬ ለገሠ