1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሊቢያ እና የአፍሪቃ አቋም

እሑድ፣ ሰኔ 12 2003

በሊቢያ መሪ ሙአመር ኧል ጋዳፊ አንጻር የሚታገሉት ዓማጽያን በቤንጋዚ ያቋቋሙት የሽግግር ብሄራዊ ምክር ቤት ካንዳንድ አፍሪቃውያት ሀገሮች ዕውቅና አገኘ።

https://p.dw.com/p/RUTe
ምስል dapd

ዕውቅና የሰጡት ሀገሮች ሴኔጋል፡ ሞሪታንያ፡ ቻድ፡ ላይቤሪያ እና ጋምቢያ ናቸው። የነዚህ አምስት አፍሪቃውያት ሀገሮች ርምጃ የአፍሪቃ ህብረት ለሊቢያ ውዝግብ በድርድር ሰላማዊ መፍትሄ እንዲፈለግ በያዘው አቋም ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ማሳረፍ መቻል አለመቻሉ በወቅቱ ብዙዎችን ማነጋገር ይዞዋል።

አርያም ተክሌ

መስፍን መኮንን