1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሊቢያ እና የጀርመን መንግስት አቋም

ማክሰኞ፣ ነሐሴ 17 2003

የሊቢያ መሪ ሞአመር ኧል ጋዳፊ የስልጣን ዘመን ማብቂያው እየተቃረበ የመጣ ይመስላል።

https://p.dw.com/p/Rhec
ምስል dapd

ብዙውን የሀገሪቱን ከፊል የያዙት በጋዳፊ አንጻር የሚዋጉት ዓማጽያን አሁን ከመዲናይቱ ትሪፖሊ መካከል ብዙውን ከፊል ተቆጣጥረዋል። የተመድ፡ የአውሮጳ ህብረት እና ዩኤስ አሜሪካ ባለፉት ስድስት ወራት ውጊያ የተካሄደባትን ሊቢያ ወደ ዴሞክራሲያዊው ስርዓት ለምታደርገው ሽግግር ፖለቲካዊና ኤኮኖሚያዊ ርዳታ እንደሚያደርጉ ሲናገሩ ተሰምቶዋል። ኔቶ በአሁን ከጋዳፊ አመራር የምትላቀቅበት ጊዜ ሩቅ አይደለም በምትባለዋ ሊቢያ ውስጥ ባካሄደው ውጊያ ያልተሳተፈው የጀርመን መንግስት ምን ዓይነት አቋም ነው የያዘው። ለበርሊኑ ወኪላችን ይልማ ኃይለሚካኤል ከጥቂት ሰዓታት በፊት ያቀረብኩለት ጥያቄ ነበር።

ይልማ ኃይለሚካኤል

አርያም ተክሌ

ነጋሽ መሀመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ