1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ልብ፤ የሰዉነት ማሽን

ማክሰኞ፣ ሰኔ 30 2001

ልብ የደም ማመላለስ ተግባርን በሰዉነት ክፍላችን እንደምታከናዉን ገና የአንደኛ ደረጃ ተማሪ ሳለ ቀለም የቆጠረ ወገን ሁሉ እንደሰማ አያጠያይቅም።

https://p.dw.com/p/Ij2y
የታመመ ልብ በቀዶ ጥገና በሌላ ሊቀየር ተይዟልምስል AP

ይህች ደም ዑደቱን ሳያቋርጥ እንዲዟዟር የምታደርገዉ የተፈጥሮ ማሽን እክል ሊደርስባት የሚችለዉ በአገልግሎት ብዛት ብቻ ሳይሆን ገና ከመወለድም የሚሆንበት ጊዜ እንዳለ የልብ ህክምና ባለሙያ የሆኑት ዶክተር በቀለ አለማየሁ ይናገራሉ። የተለያዩ ሰዎች ህይወት ሳይታሰብ በአጋጣሚ ሲያልፍ ቶሎ የሚጠየቀዉ የልብ ችግር ነበረበት ወይም ነበረባት? የሚለዉ ሲሆን ሲከሰት ድንገትነቱ ህይወትን ሊያሳልፍ የሚችልበት ሁኔታም በተደጋጋሚ ታይቷል። ይህን ከግምት አስገብተን ነዉ ልብን ስለሚገጥመዉ ጠንቅ ባለሙያዉ እንዲያብራሩልን ያደረግነዉ፤

ሸዋዬ ለገሠ/ ነጋሽ መሐመድ