1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

«ልዑል አለማየሁ» ሙዚቃዊ ተዉኔት

ሐሙስ፣ ነሐሴ 29 2006

የአዲስ አበባ የትያትር ጥበባት ተማሪዎች «ልዑል አለማየሁ» በሚል ርዕስ አዲሱን 2007 ዓመት አስታከዉ በብሔራዊ ትያትር ሙዚቃዊ ተዉኔት ለማቅረብ ዝግጅት ላይ ይገኛሉ። ታሪካቸዉ እጅግም ብዙ እንዳልተፃፈበት እና ትያትርም ሆነ ሙዚቃ እንዳልተሰራለት ስለተነገረዉ ስለ አፄ ቴዎድሮስ ልጅ ስለ ልዑል አለማየሁ ቴዎድሮስ፤

https://p.dw.com/p/1D64V
73. Jahrestag äthiopische Patrioten
ምስል DW/A. T. Hahn

ታሪክ ስለሚያወሳዉ ሙዚቃን ያካተተ ትያትር « ልዑል አለማየሁ» የለቱ መሰናዶአችን ርዕስ ነዉ።

ካሳ ኃይሉ በ1811 ዓ.ም ጥር 6 ቀን ተወለዱ፤ በ1845 የካቲት ወር አፄ ቴዎድሮስ ተብለው ነግሰው እስከ 1860 ከእንግሊዝ ጦር ጋር መቅደላ ላይ በተደረገው ውጊያ ጦራቸው በመሸነፉ ሽጉጣቸውንጠጥተዉ መሞታቸዉ ታሪክ ያሳየናል። አፄ ቴዎድሮስ እንደሞቱ የአፄ ቴዎድሮስ ልጅ ልዑል አለማየሁስምንትዓመት እንደነበር ከዝያም በእንጊሊዞች እጅ መዉደቃቸዉናወደ እንጊሊዝ መወሰዳቸዉን አቶ ነብዩ ተናግረል። ታሪክን ልናዉቅና ልንመረምር ይገባናል የሚሉት በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የሥነ-ጥበባት ኮሌጅ ዲን አቶ ነብዩ ባዬ ስለ ልዑል አለማየሁ ታሪክበመቀጠል፤

« አባቱ በእንግሊዞች እጅ መውደቅን የጠሉት ለህይወታቸው ሳይሳሱ ቀርተው አልነበረም፤ ግን የኢትዮጵያ ልዕልናም ሆኖባቸው ነዉ፡፡አፄቴውድሮስ በመቅደላ ሲወድቁ ከሁለተኛ ባለቤታቸው እቴጌ ጥሩወርቅ የሚወለደው ልዑል አለማየሁ እድሜው ስምንት ነበር፡፡ አፄ ቴዎድሮስ መቅደላ ላይ በእንግሊዞች አልያዝም ብለዉ ሽጉጥ ጠጥተዉ ከሞቱ በኋላ ልዑል አለማየሁም ከእናቱ እቴጌ ጥሩወርቅ ጋር በእንግሊዞች እጅ ወደቀ፡፡ »

በእንግሊዝ ሀገር ስደት ላይ የነበሩት የአፄ ቴዎድሮስ ልጅ ልዑል አለማየሁ በሀገር ናፍቆትበቤተሰብ በባህል ፍቅርሰቀቀን ዉስጥ እንደኖሩ የገለፁልን አቶ ነብዩ እንደ ታሪክ መረጃ በኒሞንያ በሽታ እንደሆነ ተዘግቦአል፤ በሀገር ናፍቆትም እንደሆን የፃፉ አልጠፉም ሲሉ ተናግረዋል። የልዑል አለማየሁ ተዉኔት ዋና አዘጋጅ በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የሥነ-ጥበባት ኮሌጅ ዲን አቶ ነብዩ ባዬ ፤ ያዘጋጁት ሙዚቃ ተዉኔትም ይህንኑ አጉልቶ እንደሚያሳይ የሥነ-ጥበባት ኮሌጅ ተማሪዎችና የሙዚቃዊ ተዉኔቱ ተሳታፊዎች ገልፀዋል። ።

ለቃለ- ምልልስ የተባበሩን በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የሥነ-ጥበባት ኮሌጅ አባላትን እናመሰግናለን። ሙሉዉን ቅንብር የድምፅ ማዕቀፉን በመጫን ይከታተሉ።

አዜብ ታደሰ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ