1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ልዩ ጥቅም ለአዲስ አበባ መምህራን

Merga Yonas Bulaረቡዕ፣ ሰኔ 15 2008

በአዲስ አበባ ለሚገኙ መምህራን የቤት ክራይ ድጎማ ማሻሽያ መደረጉ እና ነፃ የህዝብ ትራንስፖርት መጠቀም የምችሉበት መንገድ ማበጀቱን የአድስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አስታዉቋል።

https://p.dw.com/p/1JBSp
Addis Ababa (Äthiopien)
ምስል picture alliance/landov

[No title]

በአዲስ አበባ ዉስጥ መሚገኙ ትምህርት ቤቶች የሚያገለግሉ መምህራን እያጋጠማቸዉ ያለዉ የኑሮ ዉድነት ታሳቢ በማድረግ የቤት ክራይ ድጎማ እና የከተማ አዉቶብስን በነፃ እንድጠቀሙ፣ ለዚህም መንግስት ከ50 ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ ለማድርግ እንደተዘጋጀ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሃለፊ አቶ ድላሞ ኦቶሬ ለዶቼ ቬሌ ተናግረዋል። እንደ አቶ ድላሞ መምሃራን በአነስተኛ ዋጋ ተካራይተዉ የሚኖሩበትን ቤት ለማቅረብ አስተዳደሩ ቅድመ ዝግጅት እያደረገ መሆኑን ተናግረዋል።

በአዲስ አበባ የሚኖሩ መምህራን ይሄን የትምህርት ቢሮዉን ርምጃ እንዴ ት ይመለከቱታል ብለን ጠይቀን ነበር። በአድስ ከተማ ክፍለ ከተማ ነዋሪ የሆኑትና የድላችን ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት መምህር የሆኑት መምህር ዩሱፍ ኑርዬ ለዶቼ ቬሌ እንዲህ ሲሉ ገልፀዋል።

የቤት ግንባታዉ በመጋቢት ወር 2008 ዓ/ም ዉስጥ ስብሰባ ላይ ተነግሮን ነበር የምሉት መምህር ዩሱፍ ከግንቦት ወር ጀምሮ መንግስት ለቤት ድጎማ በወር 850 ብር እየተሰጣቸዉ መሆኑን አክለዉ ገልፀዋል። የቤቱን ግንባታ በተመለከተ አንድ አንድ አስተያየት ሰጭዎች መንግስት እንደወትሮዉ ተሰፋ ከመስጠት ዉጭ እዉን አያደርግም የሚሉ አስተያየት ሰጭዎችም አሉ።


እሄን ጉዳይ በተመለከተ በዶይቼ ቬሌ የፊስቡክ ተከታታዮች በሰጡት አስተያየት፤ የኑሮ ዉድነት በአዲስ አባባ ብቻ ስላልሆነ መንግስት ይህን በጎ ርምጃ በሃገር አቀፍ ደረጃ መፈፀም እንዳለበት አሳስበዋል።

መርጋ ዮናስ

አዘብ ታደሰ