1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሎውሮ ባግቦ በዓ/አቀፉ የጦር ወንጀል ተመልካች ፍ/ቤት

ረቡዕ፣ የካቲት 13 2005

የቀድሞው የኮት ዲቫር ፕሬዚዳንት የሎሮ ባግቦ ክስ ከነገ ጀምሮ እስከ የካቲት ሀያ ስምንት ድረስ ዴን ሀግ በሚገኘው አለም አቀፉ የጦር ወንጀል ተመልካች ፍርድ ቤት መደመጥ ይጀምራል። ባግቦ እኢአ ከ 2000-2010 ዓ ም የቀድሞው የኮት ዲቫር መሪ በነበሩበት ወቅት

https://p.dw.com/p/17gR7
ምስል picture-alliance/dpa

ለተፈፀሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በተጠያቂነት ተከሰዋል። በ67 አመቱ የቀድሞ መሪ ላይ ከተሰነዘሩ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ጥቂቶቹ የነፍስ ማጥፋት ወንጀል እና አስገድዶ መድፈር ይገኙበታል።

Elfenbeinküste Vertriebene Flüchtlinge Guiglo Afrika
ከ 300000 በላይ የሚሆኑ ከቤታቸው ተሰደዋልምስል Amnesty International


በሎሮ ባግቦ አዛዥነት ተፈፀሙ የተባሉት ወንጀሎች ሁለት አመት ሆኗቸዋል። ያኔ በሀገሪቱ በተካሄደው ደም ያፋሰሰ ግጭት ወደ 3000 የሚጠጋ ሰው ህይወቱን አጥቶዋል፣ በመቶ ሺ የሚቆጠሩ የመኖሪያ ቤታቸውን ትተው ተሰደዋል። ለግጭቱ ምክንያት የሆነው እኢአ 2010 ህዳር ወር ከተካሄደው ፕሬዜዳንታዊ ምርጫ በኋላ ባግቦ አሸናፊ ለሆኑት አላሳን ዋታራ ስልጣን አላስረክብም ማለታቸው ነበር። የህገ መንግስቱ ፍ/ቤት በባግቦ ደጋፊዎች እጅ ስለነበርም ባግቦን የምርጫው አሸናፊ አድርጎ በይፋ ገልፆ ነበር። በዋታራ እና የባግቦ ደጋፊዎች መካከል የተቀጠለው ሁከት እኢአ በ2011 በፀደይ ወራት በመባባሱም ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በኮት ዲቯር ላይ ግፊቱን ሲያጠናክር፣ የቀድሞ ቅኝ ገዢ ፈረንሳይ ወታደራዊ ርምጃ ወስዳ ባግቦን እኢአ ሚያዚያ 11 ፣ 2011 ዓ ም ቁጥጥር ስር አዋለች። ይህ ከሆነ ከአንድ ወርም በኋላ አላሳን ዋታራ የምዕራብ አፍሪቃይቱ ኮትዲቫር ፕሬዚደንት ሆነው ተሹመዋል።


በመዲናይቱ አቢዣን የጀርመናውያኑ ፍሪሪድሪሽ ኤበርት ተቋም ሰራተኛ የንስ-ኡቨ ሄትማን እንደሚሉት፣ ከነገ ጀምሮ የኮት ዲቫር መዲና ትኩረት ወደ ክሱ ወደሚደመጥበት ዴን ሀግ ይሆናል። ግን ሁሉም በአለም አቀፉ የጦር ወንጀል ተመልካች ፍርድ ቤት ስራ ደስተኛ አይደሉም።

« በትክክል ተመልክቼው ከሆን፤ ሕዝቡ የፍርዱን ሂደት የአሸናፊዎች ውሳኔ አድርጎ ነው የሚመለከተው። እና ይቃወመዋል፤ እንዳውም ባግቦን መወንጀል አይገባም ብሎ ነው የሚያስበው። በተለይ ደግሞ የባግቦ ፓርቲ ባግቦ በነፃ ይለቀቁ በሚል በያዘው አቋሙ እንደፀና ይገኛል።»
በክሱ ላይ ትችት የሚያሰሙት ወገኖች በኮት ዲቫር ለታየው አለመረጋጋት ከፍተኛ ድርሻ የነበራቸው የፕሬዚዳንት ዋታራ ደጋፊዎች በዴን ሀግ ፍርድ ቤት መቅረብ ሲገባቸው አለመቅረባቸውን ትክክለኛ ሆኖ አላገኙትም። እና ሄትማን አክለው እንዳስረዱት፣ የአንዱ አካል ተወካዮች ብቻ ፍርድ ቤት በመቅረባቸው፤ የፍርዱ ሂደት ገለልተኛ እና ሚዛናዊ ነው ለማለት እንደሚከብዳቸው ለዶይቸ ቬለ ገልፀዋል። ይህንን ወቀሳ ግን የአለም አቀፉ የጦር ወንጀል ተመልካች ፍርድ ቤት ቃል አቀባይ ፋዲ አብዱላህ አይጋሩም።

« የአለም አቀፉ የጦር ወንጀል ተመልካች ፍርድ ቤት ወንጀል ዓቃቤ ሕግ ፖሊሲ ፤ በተወሰኑ ሀገራት ለተፈተፀሙ ትልቅ ወይም እጅግ አስከፊ ወንጀሎች ተጠያቂ የሆኑትን ለፍርድ ማቅረብ ነውለ። ስለሆነም አቃቢ ህጉ ፍርድ ቤቱ ዳኞች ሊያቀርበው የሚችለው የተወሰ ክሶችን ብቻ ነው። ምክንያቱም ዋናው ሀላፊነት ያለው በአገሮቹ ብሔራዊ የፍትሕ አውታር ላይ ነው።»

የጅምላ ግዲያ፣ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እና የጦር ወንጅል ክሶችን የሚመለከተው ዴን ሀግ የሚገኘው አለም አቀፉ የጦር ወንጀል ተመልካች ፍርድ ቤት አስር አመት ሆኖታል። ፍርድ ቤቱ ከተመሰረተ አንስቶ እስካሁን በሁለት ክሶች ላይ ፍርድ ሲበይን 18 የሚሆኑ የወንጀል ክሶችን መሥርቶዋል። ከነዚህ ክሶች የባግቦ ክስ አንዱ ነው። በርግጥ በባግቦ ላይ የተመሠረተው ክስ ችሎት ከተጀመረ፤ ሎሮ ባግቦ በፍ/ቤቱ የቀረቡ የመጀመሪያው የቀድሞ አፍሪቃዊ መሪ ይሆናሉ። ከዛ በፊት ግን ነገ የሚጀምረው የክስ ማዳመጥ ሂደት እስከ ሚቀጥለው ሳምንት ሀሙስ ይቀጥላል።

Den Haag Elfenbeinküste Präsident Laurent Gbagbo vor Gericht Dezember 2011
እኢአ 2011 ሎሮ ባግቦ በአለም አቀፉ የጦር ወንጀል ተመልካች ፍርድ ቤትምስል dapd

ናዲና ሽቫርስቤክ

ልደት አበበ

አርያም ተክሌ