1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ኪነ ጥበብ

ሕገ-ወጥ አዳኞች (ገቢር 7 ከትዕይንት 1 እስከ 4)

ማክሰኞ፣ ጥቅምት 14 2010

ወንጀል ተፋላሚዎቹ! አዲስ ተከታታይ ድራማ ጽሑፍ በፌስ ቡክ። በፈጣን የሴራ ፍሰት፥ በአጫጭር ትእይንቶች የተገነባው ድራማ በአይነቱ ለየት ያለ ነው። ይኽ የድራማ ጽሑፍ በዶይቸ ቬለ የአማርኛው ክፍል የፌስቡክ ገፅ የሚቀርብ ሲኾን፤ ለሽልማት የሚያበቃ ነው። ስለ ተሳትፎ እና ውድድሩ ፌስቡክ ገጻችን ላይ በዝርዝር ይገኛል።

https://p.dw.com/p/2iHR3
09.2015 Crime Fighters MQ amharisch

ሕገ-ወጥ አዳኞች (ገቢር 7 ትዕይንት 1)

ወጣቱን የእንስሳት ሐኪም ጳዉሎስን የገደለው ማን እንደሆነ ማግኘት ይኖርብናል። ይኼ ሚ/ር ጂ የሚባለውስ ግለሰብ? መርማሪ ዓለሙ እና ከበደ ለረጅም ጊዜ ሚ/ር ጂን የማፈላለግ ልፋታቸው በስተመጨረሻ ፍሬ አፍርቶ ይሆን?

«ሚ/ር የተባለው ሰው ማን እንደሆነ ስታውቅ ምን እልክ?»

« ቆይ ቆይ አንዴ። ሚ/ር ማለት እእእ… ያ የጠረጠርነው  ነው  እንዳትለኝ ብቻ?!»

«አዎ አዎ ከበደ! ያ የጠረጠርነው  ግለሰብ ነው፤ በል አሁን ሚ/ር በጓሮ በኩል ከማምለጡ በፊት በፍጥነት ወደ ውስጥ እንግባ»

መርማሪ ዓለሙና ከበደ በድንጋጤ ፈዛ የምትመለከታቸውን ጸሐፊ አልፈው ፊት ለፊት ወደሚታየው ክፍል በጥድፊያ ያመራሉ። ጸሐፊዋ ስልኩን እንደጨበጠች በሩን በርግደው ዘው ይላሉ። ዶ/ር ሰናይት በርካታ ሰነዶች በእጇ ይዛለች።

«ሄይ! ኦፊሰር ምን እግር ጣለህ ጃል! አሁን ግን ላናግርህ አልችልም! ቆየት ብለህ ትመለስ…»

«ፍጠን ከበደ ያንን የወረቀት መሸርከቻ ማሽን አስቁመው፤ መረጃዎችን እያጠፋች ነው!»

የወረቀት መሸርከቻው ይቋረጣል።

«ዶ/ር ሰናይት ወይስ ሚ/ር ጂ? ማን ብለን እንጥራሽ? ለማንኛውም በሕገ-ወጥ የእንስሳት አደን እና በሕገ-ወጥ የዝኆን ጥርስ ንግድ ዝውውር በሕግ ቁጥጥር ስር ውለሻል፡፡»

ዶ/ር ሰናይት እጆቿ ይታሠራሉ። በንዴት ፊቷ እንደቀላ ጮኽ ብላ ትናገራለች።

«ስማ! እኔ ማን እንደሆንኩ ታውቃለህ ግን?»

«እንዴታ! አኹንማ ማን የማያውቅሽ አለ? ሚ/ር ጂ!» በይ አሁን  ቀጥዪ!»

***

ሕገ-ወጥ አዳኞች (ገቢር 7 ትዕይንት 2)

ስመ-ጥር የእንስሳት ተንከባካቢዋ ዶ/ር ሰናይት በእኩይ ምግባሩ ስመ-ገናናው ሚ/ር ጂ ትሆናለች ብሎ ማን ጠረጠረ? እሷ ራስዋ ስለ ራሷስ ምን ትል ይሆን? የምርመራው ክፍል ውስጥ መርማሪ ዓለሙ ምጸት በተሞላበት ድምፅ እያናገራት ነው።

«ዶ/ ሰናይት! የዝኖች ዋስትና ጠበቃዋ!  የዱር አራዊት እና የቱሪዝም ግብረ ኃይል ሊቀ መንበር ተሹዋሚዋ ወይስ የሕገ- ወጥ አዳኞች ንጉ / ልበልሽ?»

«ሰውዬ ምንድን ነው የምትለው? እኔ ፈጽሞ የማውቀው ነገር የለም!»

«መርማሪ ዓለሙ እባላላሁ፤ እመቤቴ!»

«ጥሩ መርማሪ እኔ መብቶቼን የማውቅ ሰው ነኝ! እንደነዛ ምስኪን እስረኞች እንዳልመስልህ! አሁን ጠበቃዬን ማግኘት እፈልጋለሁ!»

«ሟቹ፤ በአሰቃቂ ኹኔታ በስለት የተገደለው ጳዉሎስ ታውቂዋለሽ

«ማን ነው እሱ ደግሞ

«ለሚ/ የተላከ የዛቻ ደብዳቤ ግለሰቡ ኮምፒዩተር ውስጥ ተገኝቷል፡፡ አሁንስ አወቅሽው? እሱንስ ያስገደልሽው አንቺ አይደለሽም ዶ/ ሰናይ

«ይሄ የሐሰት ውንጀላ ነው!»

«መልሺልኝ! የሰው ሕይወት አጥፍተሻል አይደል /

«ጠበቃዬን ከማግኘቴ በፊት ምንም መልስ አልሰጥ

«መቼም የራስሽ ተቀጣሪ የሆኑትን ሕገ ወጥ አዳኞች በቁጥጥር ስር እንዳዋልናቸው የምታውቂ መሰለን። እነሱ ደግሞ ምን እንደሚሉ ለመስማት በጣም ጓጉቻለሁ!»!»እፈልጋለሁ ማግኘት ጠበቃዬን አልኩህ፣ አገናኘኝ ጠበቃዬን»

***

ሕገ-ወጥ አዳኞች (ገቢር 7 ትዕይንት 3)

ከጎን ባለው የምርመራ ክፍል ውስጥ፤ መርማሪ ከበደ፤ ከበርካታ የዝኆን ጥርስ ክምችታቸው ጋር እጅ ከፍንጅ የያዛቸውን ሕገ-ወጥ አዳኞች የምርመራ ቃል እየተቀበለ ነው።

«በቅድሚያ ስማችሁን እና ሥራችሁን ትነግሩን?»

«እኛ መጀመሪያ ከጠበቃ ጋር ነው መነጋገር የምንፈልገው!»

«የዝኆን ጥርሶችን አከማችታችሁ  ነው እጅ ከፍንጅ የተያዛችሁት።  ይህ በራሱ ሁለታችሁንም ወህኒ ቤት ሊያበሰብሳችሁ የሚችል ወንጀል ነው።»

«የሰማኸን አልመሰለኝም፡፡ ስለምን እያወራህ እንደሆነ አናውቅም አልንህ እኮ፡፡»

«የዝኆን ጥርሱን የትና ለማን እንደምትሸጡ፤ እንዲሁም ግብረ አበሮቻችሁ እነማን እንደሆኑ ከተናገራችሁ ፍርድ ቤት የቅጣት ማቅለያ ሊሰጣችሁ ይችላል።»

«እኔና ጓደኛዬ አደን ላይ በነበርንበት ወቅት እኔን ተኩሰህ መምታትኽ ሳያንስህ ሁለታችንንም አሰርከን። አይገርምህም? አንተኑ ገና  እከስሃለሁ!»

«አለቃችሁ ማነው?»

«እኛ አለቃ የለንም፡፡ ተራ አዳኞች ነን።»

«አለቃችሁ ሚ/ር ጂ  አይደለም? በሀሰት ስሟ ሚ/ር እየተባለች የምትጠራው የዶ/ር ሰናይት ግብረ-አበር ኾናችሁ ሕገ-ወጥ የዝኆን አደን ስትፈጽሙ ቆይታችኋል። ማወቅ ከፈለጋችሁ ደግሞ እሷንም አስረናታል! ስለዚህ የሚበጃችሁ መቀባጠሩን ትቶ እውነቱን መጋፈጥ ነው።»

ሁለቱም ሕገ-ወጥ አዳኞች በዝምታ መንሰቅሰቅ ይጀምራሉ።

***

ሕገ-ወጥ አዳኞች (ገቢር 7 ትዕይንት 4)

መርማሪ ዓለሙ ከቴሌቪዥን ጣቢያው በደረሰው መረጃ መሰረት ሚ/ር ጂ የተጋለጠበትን የቪዲዮ ምስል ለቴሌቪዥን ጣቢያው የሰጠችውን ግለሰብ ማንነት ደርሶበታል። ግለሰቧ ደግሞ በደምብ የምትታወቅ ናት፤ አሁን ዓለሙ ለሁለተኛ ጊዜ ቃሏን እየተቀበለ ነው።

«እሺ ቤቲ፤  ነገሮች እየጠሩ መሄድ ጀምረዋል።  ለምን የምታውቂውን ነገር አትነግሪንም?»

«እኔ ሠላማዊ፥ ንፁህ ሴት ነኝ አልኩህ እኮ! ስለምን እንደምታወራም የማውቀው ነገር የለም!»

«መልካም፣ እንግዲያውስ የምታውቂውን ለምን አላስታውስሽም?! አንቺና ተደራቢው ፍቅረኛሽ ጳዉሎስ ሚ/ር ጂን ስታስፈራሩት ከረማችሁ። አንቺ ደግሞ ገንዘቡን ለብቻሽ መውሰድ ስለፈለግሽ ጳዉሎስን ገደልሽው። አይደለም?» ቤቲ በድንጋጤ ዐይኗ ቦግ ይላል።

«እኔ ማንንም ሰው አላስፈራራሁም፤ ማንንም አልገደልኩም!»

«አሁን መዋሸቱ የትም አያደርስም ቤቲ! የሚስተር ጂ ማንነትን ያጋለጠውን ቪዲዮ ለቴሌቪዥን ጣቢያው አንቺ እንደሰጠሽ ደርሰንበታል። በቪዲዮ ምስሉ ላይ ሚ/ር ማለት  ዶ/ር ሰናይት መሆኗን በግልፅ ተመልክተናል።»

ቤቲ በድንጋጤ ተውጣ ቁና ቁና ትተነፍሳለች።  

«ከጳውሎስ ኮምፒውተር ውስጥ የማስፈራሪያ ደብዳቤውን፤ በላዩ ላይ ደግሞ የአንቺን የጣት አሻራዎች አግኝተናል! አሁን ጥያቄው ግድያውን ስትፈጽሚ ፍቅረኛሽ ሙሳ ተባብሮሻል ወይ ነው? ያው የዱር እንስሳት ፎቶግራፍ አንሺ ስለሆነ…» ቤቲ ማልቀስ ትጀምራለች።

«እባክህን ሙሳ ምንም የሚያውቀው ነገር የለም። ቪዲዮውንም የቀረጸው እሱ ቢሆንም እኔ ነኝ ከኮምፒዩተሩ ላይ ሰርቄ ከማስፈራሪያ የዛቻ ደብዳቤው ጋር ለሚ/ር እእእእ… ለዶ/ር ሰናይት የላኩት። ጳዉሎስን ግን እኔ አልገደልኩትም፡፡ ሙሳ ሌላው ቀርቶ ስለ ማስፈራሪያ ደብዳቤው እንኳን የሚያውቀው ነገር አልነበረም። ሁሉንም ነገር የፈጸምኩት ብቻዬን ነው።»

ቤቲ ጉንጩዋ በእንባ ይታጠባል።

***

የድራማውን ቀጣይ ክፍል ማለትም ገቢር 2 አራት ትእይንቶች ይኽን ሲጫኑ ያገኛሉ።

የድራማውን ቀጣይ ክፍል ማለትም ገቢር 3 አራት ትእይንቶች ይኽን ሲጫኑ ያገኛሉ።

የድራማውን አራተኛ ክፍል ማለትም ገቢር 4 አራት ትእይንቶች ይኽን ሲጫኑ ያገኛሉ።

የድራማውን አምስተኛ ክፍል ማለትም ገቢር 5 አራት ትእይንቶች ይኽን ሲጫኑ ያገኛሉ።

የድራማውን የመጀመሪያ ክፍል ማለትም ገቢር 6 አራት ትእይንቶች ይኽን ሲጫኑ ያገኛሉ።

የድራማውን የመጀመሪያ ክፍል ማለትም ገቢር 1 አራት ትእይንቶች ይኽን ሲጫኑ ያገኛሉ።

የድራማውን ቀጣይ ክፍል ማለትም ገቢር 8 አራት ትእይንቶች ይኽን ሲጫኑ ያገኛሉ።

ጀምስ ሙሃንዶ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

እሸቴ በቀለ