1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

መታሰቢያ ሐውልትና ቤተ-መዘክር ለቀይ ሽብር ሰለባዎች፣

ሰኞ፣ የካቲት 29 2002

በደርግ ዘመን የቀይ ሽብር ሰለባዎች የሆኑ ኢትዮጵያውያን ወላጆች፣ ያሠሩት የመታሰቢያ ሐውልት መመረቁን ፣ ከአዲስ አበባ፣ ጌታቸውተድላ የላከልን ዘገባ ያስረዳል።

https://p.dw.com/p/MNIy
ምስል AP

በመስቀል አደባባይ በተሠራው ሐውልት ዙሪያ በወቅቱ በወታደራዊው መንግሥት የተፈጸሙ እኩይ ተግባራትን የሚያስታውስ ቤተ-መዘክር አብሮ ተመርቆ ለህዝብ ክፍት ሆኗል። በዚያ ዘመን በተለይ በ 1969 ዓ ም፣ ተቃዋሚ በሆነ የፖለቲካ ድርጅት አባላት ላይ ቀይ ሽብር በሚል ሳያሜ በአዋጅ መልክ ነጻ የኃይል እርምጃ ይፋ በሆነ መመሪያ የተፈጸመ ሲሆን ህይወታቸውን ያጡት እጅግ በዛ ያሉ የተቃዋሚው ፓርቲ አባላት አኀዝ እስካሁን ከግምት በስተቀር ትክክለኛው አኀዝ አይታወቅም።

ጌታቸው ተድላ

ተክሌ የኋላ

ነጋሽ መሐመድ