1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

መክሊት መርሻና ፎቶግራፎቿ

ዓርብ፣ ግንቦት 17 2004

እኢአ 1883 ዓ ም ነው ለመጀመሪያ ጊዜ ጀርመን አገር ፎቶ መፅሄት ላይ የታተመው። ጥንት ፎቶ ማንሳት አድካሚ እና ጊዜ የሚወስድ ነበር። ይሁንና ዛሬ በ21ኛው ክፍለ ዘመን የፎቶ ካሜራ እንደልብ በሚገኝበት ፤ ስንቶቻችን ነን እንደ ቀልድ ፤

https://p.dw.com/p/1522o
Äthiopien, zwei Jungs in Awasse See am Amoragedel. Copyright: Meklit Mersha Mai, 2012 ***Nur für den Bericht über die Fotografin Meklit Mersha verwenden***
በሐዋሳ ሀይቅ አሞራ ገደል መክሊት ያነሳችው ፎቶምስል Meklit Mersha

ፎቶ ማንሳት የምንወድ? በዛሬው የወጣቶች ዓለም መክሊት መርሻ የተባለችውን ወጣት የጭውውት እንግዳችን እንድትሆን ዘንድ ጋብዘናታል። መክሊት ፎቶ ማንሳት ትወዳለች። ፎቶዎቿም ተወዳጅነት አግኝተው በቅርቡ በአንድ የጀርመን መፅሄት ላይ ይታተማሉ። «ከሰዎች ይልቅ ነፍሳትን ማንሳት ይቀለኛል» መክሊት መርሻ።

Äthiopien Schmetterlinge. Copyright: Meklit Mersha Mai, 2012 ***Nur für den Bericht über die Fotografin Meklit Mersha verwenden***
መክሊት ተፈጥሮን ስታደንቅ አግኝታ ያነሳቻት ቢራቢሮምስል Meklit Mersha

ቴክኖሎጂ በተሻሻለበት በአሁኑ ዘመን፣ የምናነሳቸውን ፎቶዎች በሰከንድ መልሰን መመልከት የምንችል ስለሆነ ፎቶ ማንሳት ከድሮ ጋ ሲነፃፀር ርካሽ እና ቀላል እየሆነ መቷል። ይሁንና ጥሩ ፎቶ አንሺ ለመሆን ከጥሩ ካሜራ ሌላ ጥሩ አመለካከት እና የግል ችሎታን ይጠይቃል። መክሊት በትርፍ ጊዜዋ ደስ የሚያሰኛትን የፎቶ ማንሳት የስራ ውጤቶች በአገር ውስጥ ለንግድ ለማዋል ጊዜ አልፈጀባትም።

የ 21 ዓመቷ መክሊት የአዲስ አበባ ነዋሪ ናት። ፎቶ ለማንሳት ስትል ወደ አዋሳ እና ሌሎች ከተሞችም ወጣ ማለት ታዘወትራለች። ስለ ፎቶ አነሳስ ስታወጋን« ከሰዎች ይልቅ ነፍሳትን ማንሳት ይቀለኛል» አለች። ለምን እንደሆነ አጫውታናለች። ሙሉ ጭውውቱን ከዘገባው ያድምጡ።

ልደት አበበ

ተክሌ የኋላ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ