1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

መድኃኒት የተላመደው የሳንባ ነቀርሳ በኢትዮጵያ

ሐሙስ፣ መጋቢት 15 2003

በኢትዮጵያ መድሐኒት በተላመደው ሳንባ ነቀርሳ የተጠቁ ህሙማንን ለማከም ባለፈው አንድ ዓመት በተደረገው ጥረት ከአምናው የተሻለ ውጤት ቢገኝም አሁንም ህክምና ያልጀመሩ ህሙማን እንዳሉ ተገለፀ ።

https://p.dw.com/p/RCKX
የሳንባ ነቀርሳ በሽተኛምስል AP

ለበሽታው ህክምና በሚሰጥበት በብቸኛው የቅዱስ ጴጥሮስ ሆስፒታል በዚህ በሽታ ላይ ክትትል የሚያደርገው ቡድን መሪ ዶክተር ዳንኤል መረሳ ለዶቼቬለ እንዳስረዱት ፣ ባለፉት አንድና 2 ዓመታት ፤ ሁለት መቶ ታካሚዎች መድኃኒት ማግኝት ችለዋል ። የተወሰኑ ደግሞ ህክምና ለመጀመር ተራቸውን እየተጠባበቁ ነው ። የሳንባ ነቀርሳ መንስኤ የሆነው TB bacilus በጀርመናዊው ሳይንቲስት በዶክተር ሮበርት ኮኽ ከታወቀ ዛሬ 129 ዓመት ቢሞላውም አሁንም በርካታ ሰዎች በበሽታው ህይወታቸው ማለፉ አልቀረም ። ከዛሬ 2 ዓመት በፊት እንኳን በዚህ በሽታ ቁጥራቸው 1.7 ሚሊዮን ሰዎች ሞተዋል ። ከተወሰኑ ዓመታት ወዲህ ደግሞ መድኃኒት የተላመደው የሳንባ ነቀርሳ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንደሚባለው ሆኖ በሽታውን ለመከላከል ብሎም ለማጥፋት በተጀመረው ጥረት ላይ ተጨማሪ ዕንቅፋት ሆኗል ። ዛሬ የሚታሰበውን የዓለም የሳንባ ነቀርሳ ቀን ምክንያት በማድረግ የዓለም የጤና ድርጅት ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው በመጪዎቹ 5 ዓመታት መድኃኒት በተላመደው ሳንባ ነቀርሳ የሚያዙ ከ 2 ሚሊዮን በላይ አዳዲስ በሽተኞች ይኖራሉ ተብሎ ይገመታል ። የዚህ ችግር ተጠቂ በሆነችው በኢትዮጵያም ቁጥራቸው ጥቂት የማይባል ህሙማን እንዳሉ ዶክተር ዳንኤል መረሳ በቅዱስ ጴጥሮስ ሆስፒታል በበሽታው ላይ ክትትል የሚያደርገው ቡድን መሪ ለዶቼቬለ አስረድተዋል ። ድምፅ እንደ ዓለም ጤና ድርጅት መድኃኒት በተላመደው ሳንባ ነቀርሳ የተያዙ ህሙማን ቁጥር ከ3 ዓመት በፊትወደ 440 ሺህ ይደርስ ነበር ከነዚህም 150 ሺው ህይወታቸው አልፏል ። ዶክተር ዳንኤል እንደሚሉት ችግሩ የዚህ ዓይነቱ የሳንባ ነቀርሳ መድኃኒት ዋጋ መወደድና ህክምናውንም ቀላል አለመሆኑ ነው ። ያም ሆኖ ዶክተር ዳንኤል እንደሚሉት በኢትዮጵያ መድኃኒቱን ለህሙማን ለማዳረስ ጥረት እየተደረገ ነው ። ድምፅ በርካታ የሳንባ ነቀርሳ ህሙማን በሚገኙባት እንደ ኢትዮጵያ በመሳሰሉ ሀገራት በሽታውን ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት ለማሳካት ተጨማሪ የገንዘብ እርዳታ ያስፈልጋል ። አለበለዚያ ግን እስካሁን የተገኘው ውጤት ወደ ኃላ ተቀልብሶ የኃሊት ጉዞ መጀመሩ የማይቀር እንደሚሆን የዓለም የጤና ድርጅት ያስጠነቅቃል ። ባለሞያው ዶክተር ዳንኤል ደግሞ ህብረተሰቡ በሽታውን መከላከል ላይ እንዲያተኩር ይመክራሉ ። ድምፅ

Tuberkulöse Lunge von Tuberkel-Bakterien
TB bacilus ባክቴሪያምስል dpa
BdT Robert Koch in seinem Labor
ዶክተር ሮበርት ኮኽምስል Robert-Koch Stiftung

ሂሩት መለሰ

አርያም ተክሌ