1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

መፍትሄ ያላገኘው የአውሮፓ ስደተኞች ቀውስ

ረቡዕ፣ መስከረም 5 2008

የአውሮፓ የስደተኞች ቀውስ የመገናኛ ብዙኃንን ትኩረት መሳቡ ቀጥሏል። እንደ የአውሮፓ ህብረት የድንበር ተቆጣጣሪ ድርጅት-ፍሮንቴክስ አዲስ መረጃ ከሆነ ካለፈው ጥር ወር አንስቶ እስከ ነሐሴ ድረስ ከ 500 000 በላይ ስደተኞች በአውሮፓ ህብረት አባል ሃገራት ገብተዋል።

https://p.dw.com/p/1GXRo
Ungarn Horgos Grenze Flüchtlinge
ምስል Reuters/M. Djurica

[No title]

ባለፈው በጎርጎሮሳዊው 2014 ዓመተ ምህረት በጠቅላላው ወደ አውሮፓ የገቡት 280 000 ገደማ ነበር።አለም አቀፉ የስደተኞች ጉዳይ ድርጅት በምህፃሩ IOM ባለፉት 8 ወራት ወደ አውሮፓ ከመጡት ስደተኞች መካከል 430 000 ያህሉ አውሮፓ የገቡት የሜዲትራኒያንን ባህር አቋርጠው ነው ይላል። እልባት ስላላገኘው የአውሮፓ የስደተኞች ቀውስ ብራስልስ የሚገኘውን ዘጋቢያችንን ገበያው ንጉሴን አነጋግረናል።

ገበያው ንጉሴ

ልደት አበበ

ሂሩት መለሰ