1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሙስና በኢትዮጲያ

Merga Yonas Bulaማክሰኞ፣ ጥር 24 2008

ትራንስፓሬንሲ እንቴርናሽናል በየሐገራቱ ያለዉን የሙስና መጠን ለመለየት ሁለት አይነት መንገዶችን ይከተላል።የመጀመሪያዉ ለየሐገራቱ የሚሰጠዉ ከዜሮ እስከ መቶ የሚደርስ ነጥብ ነዉ።ዜሮ የሚያገኙ ሐገራት ከመጨረሻዉ የሙስና ጠገግ ላይ የሚገኙ ሲሆኑ፤ መቶ የሚያገኙ ባንፃሩ ከሙስና የፀዱ ናቸዉ።

https://p.dw.com/p/1Ho5d
Logo Transparency International

[No title]

በዘንድሮዉ ዘገባ ሶማሊያ በስምንት ከመቶ የመጨረሻዉ ደረጃ ላይ ስትገኝ፤ ቦትስዋና በ63 ከመቶ የተሻለ ደረጃ ላይ ትገኛለች። ኢትዮጵያ ሰላሳ ሰወስት ከመቶ ነዉ ያገኘችዉ።


ሁለተኛዉ መመዘኛ ሐገራት በየነጥባቸዉ የሚሰጣቸዉ ደረጃ ነዉ።አንደኛ ደረጃ ከሙስና የፀዳ ሲሆን፤ የመጨረሻዉ ደግሞ ሙስና የተንሰራፋበት ማለት ነዉ።ዘንድሮ 168 ሐገራት ናቸዉ በጥናቱ የተካተቱት።ከነዚሕ ሐገራት ኢትዮጵያ 103ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች።ይህ ማለት ኢትዮጵያ ሙስና በከፍተኛ ደረጃ ከተንሰራፋባቸዉ ሐገራት አንዷ መሆንዋን አመልካች ነዉ-ይላል ዘገባዉ።


ሙስናን በቁጥር መግለፅ ከባድ እንደሆነ የትራንስፓሬንስ እንቴርናሽናል አካል የሆነዉ ትራንስፓሬንሲ ኢትዮጲያ ዋና ስራ አስከያጅ አቶ ክብሬአብ አቤራ ለዶቼ ቬሌ ይናገራሉ። የኢትዮጲያ ያስመዘገበችዉ መመዘኛ ነጥብ ሳይቀየር ደረጃዋ ከ113 ወደ 103 የመጠችበትን ምክንያት አቶ ክብሬአብ ሲያብራሩ ከኢትዮጲያ ቀድሞ የነባሩ 10 ሌሎች አገሮች ወደ ሓላ በመሸራተታቸዉ ምክንያት መሆኑን ይጠቅሳሉ። በአገሪቱ ዉስጥ የሙስና መንሴኤ ነዉ ተብሎ የሚወሰዱት ላይ ተለቅ ያለ ጥናት እንደሚያስፈልግ ከተናገሩ በዋላ ይሁን እንጂ በዋናነት ሙስና የሚታይባቸዉን አከባብዎች የህዝብ አገልግሎት ሰጭ ተቋሞች መሆኑን ጨምሮ ይናገራሉ።

Karte Äthiopien englisch

ከሰሃራ በታች ያሉት አፍርቃ አገሮች የገንዘብ አስተዳደርን በተመለከተ አልፎ አልፎ ግልፅነት የሚታይባቸዉ አገራት እንዳሉ ዘገባዉ ጠቅሶ፤ ይሁን እንጂ ሙስና የዜጎችን ፍትህ እና ደንህነትን እንደነፈገ ያትታል። ሙሰኛ የሆኑትን የመንግስት ባለስልጣናት ለህግ ማቅረብ እንዳልተሳካ እና ሙስናን በሚያጋልጡ ዜጎች ላይ ማስፈራርያዎች እንደሚዳርስባቸዉ ይህ ዘገባዉ ያመለክታል።


በኢትዮጲያም ቢሆን በአገሪቱ የወንጀል መቅጫ ህግ ያለአግባብ ጉዳይን ማንጓተት እራሱን የቻለ የሙስና ወንጀል አድርጎ እንደሚያስቀምጥ አቶ ክብሬአብ ይናገራሉ። ዘገባዉ ግልፅነት፣ ፍትህ እና የህግ የበላይነት እጦት ለዝህ ሁሉ ችግር መንሴ መሆኑን ያትታል፣ በኢትዮጲያም ብሆን የአስተዳደር ፍትህ ጉዲላት እንዳለ አቶ ክብሬአብ ይናገራሉ።

ሙስናን በኢትዮጵያ ያለበትን ደረጃ በተመለከተ በዶቼ ቬሌ የፌስቡክ ገጽ በተደረገዉ ዉይይት አብዛኞቹ ተሳታፍዎች የመልካም አስተዳደር እና የፍትህ እጦት ሙስናን እያባባሰ መሆኑን ይጠቅሳሉ።

መርጋ ዮናስ

ነጋሽ መሃመድ