1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሙስና እና የመንግሥት ፀረ ሙስና ርምጃ

እሑድ፣ ጥር 14 2009

በየዓመቱ በየሃገራቱ ያለዉን የሙስና መጠን ደረጃ የሚዘረርዝ ዘገባ የሚያወጣዉ ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል የተባለዉ ተቋም  ከፍተኛ ሙስና ከሚፈፀምባቸዉ ሃገራት አንዷ ኢትዮጵያ መሆኗን ያመለክታል።

https://p.dw.com/p/2W9A5
Geldscheine
ምስል DW/E. Bekele Tekle

AMH Diskussionsforum 22.01.2017 (Korruption in Äthiopien) - MP3-Stereo

በቀድሞዉ የደቡብ አፍሪቃ ፕሬዝደንት ታቦ ኢምቤኪ መሪነት የተካሄደ ሌላ ጥናትም በአምስት ዓመታት ዉስጥ ብቻ ከኢትዮጵያ ሕገ ወጥ በሆነ መንገድ 10 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር ወደ ዉጭ ሸሽቷል የሚል ጥናቱን ያፋ አድርጓል። የኢትዮጵያ መንግሥት ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ሙስናን ለመዋጋት ቆርጬ ተነስቻለሁ ሲል ይደመጣል። ለርምጃዉ ማሳያም ከሙስና ጋር በተገናኘ መረጃ አግኝቼባቸዋለሁ ያላቸዉን ከአንድ መቶ የሚበልጡ ግለሰቦች ማሰሩን አስታዉቋል። በሀገሪቱ ሙስና መዋቅራዊ ሆኗል የሚሉት ጉዳዩን በቅርበት የሚያስተዉሉ ወገኖች ገዢዉ ፓርቲ ሙስናን ለማጥፋት ተጀምሯል በሚለዉ ዘመቻዉ ቁርጠኝነቱን ገና አላሳየም። የእስሩ ርምጃም ቅርንጫፎች እንጂ ግንድና ሥሩ ላይ አላነጣጠረም ሲሉ ይተቻሉ።  ሙሉ ዉይይቱን ከድምጽ ዘገባዉ ያድምጡ

ሸዋዬ ለገሠ

ልደት አበበ