ማህበራዊ የጤና መድን አገልግሎት
እሑድ፣ ጥር 7 2009ማስታወቂያ
በዚሁ አዋጅ 690/2002 መሰረት፣ በአሁኑ ጊዜ በሃገሪቱ ሶስት ዓይነት የጤና መድን ዋስትና(ኢንሹራንስ) አገልግሎት ስርዓት አሉ። ከሶስቱ አንዱ የሆነው ሁሉንም የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ሰራተኞችን እና የጡረታ ባለመብቶችንም እንዲያቅፍ የተዘጋጀው ማህበራዊ የጤና መድን ሽፋን ነው። ሌሎቹ የግል እና የማህበረሰባዊ የጤና መድን አገልግሎቶች ናቸው። በኢትዮጵያ ተግባራዊ ይሆናል ተብሎ ሲጠበቅ የነበረው ማኅበራዊ የጤና መድን አገልግሎት እክል እንዳጋጠሙት ተነግሮዋል። ይኸው በመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ሊጀመር የታሰበው እና ግዴታን መሰረት ያደረገው ማኅበራዊ የጤና መድን ሥርዓት ከሁለት ዓመት በፊት ነበር በስራ ላይ መዋል የነበረበት። የዛሬው ውይይት አገልግሎቱ ያልተጀመረበትን ምክንያት እና የአገልግሎቱ የወደፊት ይዞታን ይመለከታል።
አርያም ተክሌ
ልደት አበበ