1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ማኪ ሳል ማን ናቸው?

ማክሰኞ፣ መጋቢት 18 2004

ባለፈው እሁድ በሴኔጋል በተካሄደው ሁለተኛ ዙር ፕሬዚደንታዊ ምርጫ -ማኪ ሳል ቀጣዩ የአገሪቷ ፕሬዚዳንት ሆነው ተመረጡ። ለሦስተኛ ጊዜ በዕጩነት የቀረቡት የሰማንያ አምስት ዓመቱ ፕሬዚደንት አብዱላይ ዋድ ሽንፈታቸውን ተቀብለዋል።

https://p.dw.com/p/14SSL
Opposition presidential candidate and former Prime Minister Macky Sall casts his vote at a polling station in Fatick, Senegal Sunday, March 25, 2012. Senegalese voters are deciding Sunday whether to give their 85-year-old president, Abdoulaye Wade, another term in office, or instead back his one-time protege Sall in a runoff election that could oust the incumbent of 12 years.(Foto:Tanya Bindra/AP/dapd).
ማኪ ሳልምስል AP

ባለፈው እሁድ በሴኔጋል በተካሄደው ሁለተኛ ዙር ፕሬዚደንታዊ ምርጫ -ማኪ ሳል ቀጣዩ የአገሪቷ ፕሬዚዳንት ሆነው ተመረጡ። ለሦስተኛ ጊዜ በዕጩነት የቀረቡት የሰማንያ አምስት ዓመቱ ፕሬዚደንት አብዱላይ ዋድ ሽንፈታቸውን ተቀብለዋል።

ሴኔጋል ውስጥ በርካቶች አብዱላይ ዋድ ሽንፈታቸውን ተቀብለው ስልጣናቸውን ያስረክባሉ ብለው አልጠበቁም ነበር። ዋድ በሥልጣን ለመቆየት ያደረጉት ጥረት ባለፉት ሣምንታት በሀገሪቱ ሁከት ፈጥሮ ሰንብቷል። ምንም እንኳን የምርጫው የመጨረሻ ውጤት ነገ ወይም ረቡዕ ይፋ ይወጣል ተብሎ ቢጠበቅም ተፎካካሪያቸው የተቃዋሚ ፓርቲ ዕጩ ማኪ ሳል በበርካታ የምርቻ ጣቢያዎች በከፍተኛ የመራጭ ድምፅ ሳይመረጡ እንዳልቀሩ ይገመታል። ፕሬዚደንት ዋድ በመዲናዋ ዳካር ሳይቀር በምርጫው እንደተሸነፉ ነው የተሰማው።

Senegalese President Abdoulaye Wade tours downtrodden suburban areas on the outskirts of Dakar, Senegal Wednesday, March 21, 2012, days ahead of Senegal's presidential run-off election. Senegal's aging leader will face his former protege Macky Sall in a runoff election on Sunday, March 25. Opposition leaders have united behind Sall in an effort to put an end to Wade's bid for a controversial third term as president. (Foto:Rebecca Blackwell/AP/dapd)
የሴኔጋል እኢአ 2012 ዓ ም ምርጫምስል AP

የእርሳቸው ድል የሴኔጋል ህዝብ ጭምር ድል መሆኑ የገለጹት በሙስና አንጻር ባደረጉት ትግላቸው የሚታወቁት የአገሪቷ ጠንካራ የተቃውሞ ፖለቲከኛ ማኪ ሳል እንዳስታወቁት፣ በሳቸው የስልጣን ዘመን ያለአግባብ ገንዘብ አይባክንም።

« የኛ አገር ዲሞክራሲ የሰፈነባት ናት። ኃላፊነት የተሞላው ውሳኔ የሚወስዱ የበሰሉ ዜጎች አሉን።»

መረጋጋት የሰፈነባት አገር በመሆን በምትታወቀው ሴኔጋል በበምርጫ ዘመቻው ወቅት ታይቶ የነበረው አለመረጋጋት አሁን ያበቃ ይመስላል።

ማኪ ሳል ምርጫውን ሊያሸንፉ ለቻሉበት ሁኔታ የተለያዩ ምክንያቶች ይጠቀሳሉ። በመጀመሪያ ህዝቡ የአብዱላይ ዋድ የስልጣን ዘመን በመሰላቸቱ ነው። ሌላኛው ምክንያት ዋድ ልጃቸው ካሪም እንዲተኩዋቸው ለማድረግ ያደረጉት ሙከራ ብዙዎችን አላስደሰተም።

ማኪ ሳል እአአ ከ2001 ዓም አንስቶ አሁን በተሸነፉት ፕሬዚደንት ዋድ የሥልጣን ዘመን በርካታ ጊዜያት በሚንስትርነት፣ በመጨረሻም እአአ በ2004 የአገሪቷ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው አገልግለዋል። ማኪ ሳል በ2008 ዓም በሙስና የተጠረጠሩት ከፍተኛ የመንግሥት ሥልጣን ይዘው የነበሩት የፕሬዚዳንት ዋድ ልጅ ካሪም በምክር ቤት የሙስና ኮሚቴ ፊት ለምርመራ እንዲቀርቡ ማድረጋቸውና ፕሬዚዳንቱን ክፉኛ ማስቆጣታቸው ይታወሳል፣ በዚሁ ሰበበ በስራቸው ላይ እክል ሲበዛባቸው ሳል ሥልጣናቸውን በመልቀቅ የተቃውሞውን ወገን በመቀላቀል አዲስ ፓርቲ መስርተው መንቀሳቀስ ጀመሩ።

A supporter of Senegalese opposition presidential candidate Macky Sall celebrates in the capital Dakar March 25, 2012. Senegal's President Abdoulaye Wade admitted defeat in Sunday's election, state television reported, ending his bid for a third term that had sparked deadly clashes in the normally peaceful country. The octogenarian leader phoned rival Macky Sall to congratulate him, state broadcaster RPS reported late on Sunday, an announcement greeted by celebrations across the capital Dakar. REUTERS/Joe Penney (SENEGAL - Tags: POLITICS ELECTIONS)
ምስል REUTERS

ማማዱ ባጂ፤ የማኪ ሳል የምርጫ ዘመቻ አስተባባሪ ናቸው። የምርጫው ውጤት ሴኔጋል ወደ ትክክለኛ መንገድ መጓዝ መጀመሯን ያንፀባርቃል ሲሉ ነው የገለፁት።

« በመጀመሪያው የምርጫ ዙር አብዱላይ ዋድ ናቸው ያሸነፉት። ተመስገን በአሁኑ እንደዛ አይደለም። አሁን የእውነት ኃይል የገንዘብ ኃይልን አሸንፏል ለማለት ይቻላል።»

የማኪ ሳል ስኬት በርካታ የአገሪቱ ህዝብን ቢያስደስትም ህዝቡ ብዙ ይጠብቅባቸዋል። 2/3ኛው የአገሪቱ ህዝብ በቀን ከሁለት ዶላር ባነሰ ገንዘብ ነው የሚኖረው። የወጣቶች ንቅናቄ ቡድን አባል የሆነው አልዮ ሳኔ እንደሚለው፣ የሕዝቡ መሰረታዊ ፍላጎት መሟላት ይኖርበታል። « ለማህበራዊ ችግሮች ትኩረት ሰጥቶ መፍትሔ መሻቱ ለማኪ ሳል ፈታኝ ጉዳይ ይሆናል። በተለይ የምግብ ዋጋ ሊቀንስ ይገባዋል። ከዚህ በተጨማሪ የተበላሸው የመንግሥቱ አስራር መወገድ ይኖርበታል። የሚጠብቃቸው ከባድ ጊዜ ነው፣ የሚዝናኑበት ጊዜ አይኖርም።»

ልደት አበበ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ