1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ማዕከላይ አፍሪቃ ሬፓብሊክ እና ጀርመን

ቅዳሜ፣ መጋቢት 6 2006

ወደ ማዕከላይ አፍሪቃ ሬፓብሊክ የተጓዙት የጀርመን የልማት ትብብር ሚንስትር ጌርድ ሚውለር ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የእርስበርስ ጦርነት ያመሰቃቀላንት የማዕከላይ አፍሪቃ ሬፓብሊክ ሲቭል ሕዝብ ስቃይ የማብቃት ኃላፊነት በቸልታ ማለፍ እንደማይገባው አሳስቡ።

https://p.dw.com/p/1BQ6i
ምስል picture-alliance/dpa

የማዕከላይ አፍሪቃ ሬፓብሊክ ፀጥታ አሁንም እጅግ አሳሳቢ እንደሆነ ይገኛል። በዓለም አቀፍ የርዳታ ድርጅቶች ግምት መሠረት፣ ከ700,000 የሚበልጥ ሕዝብ በዚያ በቀጠለው የኃይል ተግባር ሰበብ ተሰዶዋል ወይም ተፈናቅሎዋል። ግዙፉን የሰብዓዊ ቀውስ በቦታው በመገኘት ለመመልከት የጀርመን የልማት ትብብር ሚንስትር ጌርድ ሚውለር ከትናንት በስቲያ ወደ መዲናይቱ ባንጊ ተጉዘዋል። ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የርስበርስ ጦርነት ያመሰቃቀላንት የማዕከላይ አፍሪቃ ሬፓብሊክ ሲቭል ሕዝብ ስቃይ የማብቃት ኃላፊነት እንዳለበት አሳስበዋል።

Entwicklungsminister Gerd Müller in der Zentralafrikanischen Republik
ምስል picture-alliance/dpa

« በእዚህችው ሀገር የሚታየውን ችግር እንዳላየ አይተን ማለፍ አንችልም፣ አይገባምም። ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በዚህ የሚታየውን የሕዝቡን ግዙፍ ስቃይ እና ችግር በዝምታ ማለፍ የለበትም። ሕዝቡን የመርዳት አቅምም አለን። »

የጀርመን መንግሥት ለአፍሪቃ በዓመቱ የሚሰጠውን የልማት ትብብር ርዳታ ወደ 1,3 ሚልያርድ ዩሮ ለማሳደግ እንደሚፈልግ ያስታወቁት ጀርመናዊው ሚንስትር ጌርድ ሚውለር ሀገራቸው የርስበርስ ጦርነት ላመሰቃቀላት ማዕከላይ አፍሪቃ ሬፓብሊክ መርጃ ከፊታችን ሚያዝያ ወዲህ በብዙ ሚልዮን ዩሮ እንደምትሰጥ አመልክተዋል። የሚሰጠው አስር ሚልዮን ዩሮ በሀገሪቱ የተስፋፋውን የምግብ አቅርቦቱን አስተማማኝ ለማድረግ እና ለመሠረተ ልማት እንዲውል የታሰበ ነው። ከዚህ በተጨማሪ የስደተኞቹ ጉዳይ የጀርመን የልማት ትብብር መስሪያ ቤት ትኩረት የሚሰጠው ጉዳይ መሆኑን ሚንስትሩ አስታውቀዋል።

« የስደተኞች ችግር ከትልቆቹ ተግዳሮቶች አንዱ ሆኖ አየዋለሁ። የህልውና ጥያቄ በመሆኑ ትልቅ ትኩረት የምሰጠው ጉዳይ ይሆናል። የልማት ትብብር ስደተኞቹን ባፋጣኝ መርዳት እና የተሻለ የወደፊት ዕድል እንዲኖራቸው በሚያስችል መዋቅር መዘርጋት ስራ ላይ ያተኩራል።

Zentralafrikanische Republik Unruhen 26.02.2014
ምስል Reuters

ከምግብ እጥረት ጎን የፀጥታው ሁኔታ ትልቅ ችግር ደቅኖዋል። በቀድሞ ሴሌካ ዓማፅያን አንፃር የሚንቀሳቀሱት እና ሽብራቸውን ያስፋፉት ወጣቶቹ ክርስትያን የፀረ ባላካ ሚሊሺያ ቡድን አባላት በሀገሪቱ በተሰማሩትa እና በምሕፃሩ ሚስካ በመባል በሚታወቁትአፍሪቃ ህብረት ሰላም አስከባሪ ኃይላት እና በፈረንሣይ ወታደሮች አንፃር ጥቃት የሚሰነዝሩበት ድርጊት ፀጥታውን አበላሽቶታል። ቡድናቸው እንደ ጠላት እንደሚመለከታቸው ነው ቃል አቀባዩ ኤሞስዮን ጎሜስ የገለጹት። ሰላም አስከባሪዎቹ ካለፉት አራት ሳምንታት ወዲህ ባካሄዱት አሰሳ ሚሊሺያዎቹ የደበቁትን ጦር መሳሪያ መያዝ ቢሳካላቸውም የፀጥታው ሁኔታ አለመሻሻሉ የሚስካ መሪ ማርቲን ቱመንታ ገልጸዋል።

« ሁሉን አልተቆጠጠርንም። ተቆጣጥረናል ለማለት አልፈልግም። የሀገሪቱን ፀጥታ ሁኔታ ለማሻሻል ተጨማሪ ወታደሮች ያስፈልጋሉ። »

የተመድ ዋና ፀሐፊ ፓን ኪ ሙን ወደ እዚህችው ሀገር ተጨማሪ 1,000 ወታደሮች እንዲላኩ ተማፅኖ ማሰማታቸው ይታወሳል። የአውሮጳ ህብረትም በእዚህችው ሀገር ሊጀምረው ላቀደው የጋራ ወታደራዊ ተልዕኮ ወታደሮች ለማሰባሰብ ከብዙ ሳምንታት ወዲህ ያደረገው ጥረቱ እስካሁን ውጤት አልባ እንደሆነ ነው የሚገኘው።

አድሪያን ኪርሽ/አርያም ተክሌ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ