1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ማይክሮ-ክሬዲት በኢትዮጵያ

ረቡዕ፣ ሚያዝያ 5 2003

የማይክሮ-ክሬዲት ወይም የአነስተኛ ብድር አሰጣጥ ጽንሰ-ሃሣብ ከታዳጊው ዓለም ከራሱ የመነጨ አንዱ የድህነት መታገያ ዘዴ ነው።

https://p.dw.com/p/RHcD
ምስል DW-TV

የተነሣበትና ከአራት አሠርተ-ዓመታት በላይ የያዘው ዋና ዓላማም ድሆችን በተለይም በአብዛኛው ሴቶችን በሕብረተሰብ ውስጥ ማጠናከር መሆኑ ይታወቃል። ይሄው ማይክሮ-ክሬዲት ዛሬ በኢትዮጵያም ከመደበኛ ባንኮች ገንዘብ መበደር ለማይችሉ ሴቶችም የሚሰጥ ሲሆን ተግባሩን ከሚያራምዱት ግብረ-ሰናይ ድርጅቶች አንዱ በአሕጽሮት ራሴድ በመባል የሚታወቀው የሴቶች ራስ አገዝ ድርጅት ነው። ዕርምጃው ምን ይመስላል? የዚሁ ድርጅት ዓባል የሆኑ ራሳቸውን ለመቻል የበቁ ሁለት ሴቶችን ወሮ/ውዴ ደሣለኝንና ወሮ/ሕይወት ማሞን አነጋግረናል።

መሥፍን መኮንን

ሂሩት መለሰ