መራሂተ-መንግሥት አንጌላ ሜርክል ለአራተኛ የስልጣን ዘመን ይወዳደራሉ
ሰኞ፣ ኅዳር 12 2009ማስታወቂያ
ባለፉት ወራት መራሂተ መንግሥትዋ እንደሚወዳደሩ መናገራቸውን የውስጥ አዋቂ ምንጮችን ጠቅሶ ሲኤን ኤን የዜና አገልግሎት በሰፊዉ ዘግቦ ነበር። ሜርክል በሚቀጥለው ወር በሚካሔደው የወግ አጥባቂው ክርስቲያን ዴሞክራቶች ፓርቲ ዓመታዊ ጉባዔ ላይ የ62 አመቷ አንጌላ ሜርክል ራሳቸውን በእጩነት እንደሚያቀርቡም ታዉቋል። የፊዚክስ ባለሙያዋ አንጌላ ሜርክል ወደ መራሒተ መንግሥትነት የመጡት በጎርጎሮሳዊው 2005 ዓ.ም. ሲሆን የመጀመሪያዋ የጀርመን ሴት መሪ ናቸው።
አዜብ ታደሰ
ነጋሽ መሐመድ