1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሜሽካርት-የኢትዮጵያውያኑ ድረ-ገጽ መገበያያ

ዓርብ፣ ታኅሣሥ 29 2008

በሁለት ወጣት ኢትዮጵያውያን የተመሠረተው ሜሽካርት ድረ-ገጽ መገበያያ፤ የኢትዮጵያ ቡና፣ ሽሮ፣ በርበሬ፤ አልባሳት፤ መጻሕፍት፤እና መጽሄት እንዲሁም በርካታ ቁሳቁሶች የሚሸጡበት ድረ-ገጽ ነው። ወጣቶቹ በአሜሪካን በተማሩበት ዘርፍ ሥራ ማግኘት ቀላል እንዳልሆነ ይናገራሉ።

https://p.dw.com/p/1HaTU
Symbolbild E-Commerce Konzept
ምስል Fotolia/Helder Almeida

ሜሽካርት-የኢትዮጵያውያኑ የድረ-ገጽ መገበያያ

አነስተኛ ዋጋ፣ ሰፊ ምርጫ፣ ፈጣን አቅርቦት ታዋቂው የድረገጽ የግብይት መድረክ አማዞን የሚታወቅበት መርኁ ነው። የዛሬ የወጣቶች ዓለም ትኩረታችን ግን ስለ አማዞን አይደለም። አሜሪካን ሀገር በሚኖሩ ሁለት ኢትዮጵያውያን ስለ ተመሰረተው ሜሽካርት የድረገጽ ገበያ እንጂ። ሽሮ፣ በርበሬ፣ አልባሣት፣ የሙዚቃ እና የፊልም ሲዲዎች ስለሚሸጡበት የድረገጽ ገበያ ነው የምናወሳው። ሜሽካት የድረገጽ ገበያ በአሜሪካን ከ25 ግዛቶች በየጊዜው ትዕዛዝ ይቀበላል። ግብይቱ በተፈጸመ በ2 ቀናት ውስጥ የገዢው መኖሪያ ድረስ ዕቃው እንደሚደርስ መሥራቾቹ ይናገራሉ። የዋሽንግተኑ ወኪላችን ናትናኤል ወልዴ ወጣቶቹን አነጋግሮ የሚከተለውን ዘገባ ልኮልናል።

ናትናኤል ወልዴ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ነጋሽ መሐመድ