1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ምስራቅ ሊቢያ በቦንብ ተደበደበች

ማክሰኞ፣ መጋቢት 6 2003

ምስራቃዊ ሊቢያ ውስጥ ሰኞ መጋቢት 5 ቀን 2003 ዓ.ም. የመንግስት ወታደሮች አስጃዲያ የተሰኘችውን ከተማ በቦንብ መደብደባቸው ተዘገበ። እንደ አይን እማኞች ከሆነ፤ በቦንቡ ጥቃት አንድ ሆስፒታልና የከተማው ውሃ ማጠራቀሚያ ጋን ሲመታ በርካታ ሰላማዊ ሰዎች መሞታቸውና መቁሰላቸው ተገላጿል።

https://p.dw.com/p/R9Qm
የሊቢያ አማፂያን በታንክ ላይ
የሊቢያ አማፂያን በታንክ ላይምስል dapd

ተቃማሚዎች በሊቢያ መንግስት የሚደርሰውን የአየር ጥቃት ለማስቆም ዓለም አቀፉ ማኅበረ-ሰብ ሊቢያ ላይ የበረራ እገዳ እንዲጥል ተማፅነዋል። በአንጻሩ የሊቢያ መንግስት ቻይናና ሩሲያን ጨምሮ የተለያዩ ሀገራትን ለመዋዕል-ንዋይ ፍሰት በማግባባት ላይ መሆኑ ተጠቅሷል። ቻይናና ሩሲያ ድምፅን በድምፅ የመሻር መብት እንዳላቸው የሚታወቅ ነው። የሊቢያን ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ ማንተጋፍቶት ስለሺ የሚከተለውን አጠናቅሯል።

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ነጋሽ መሐመድ