1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሞልዲቭና የአየር ጠባይ ለዉጥ

ማክሰኞ፣ ሐምሌ 28 2001

የአየር ጠባይ ለዉጥ በሚያስከትላቸዉ የተፈጥሮ አደጋዎች ምክንያት ከቤት ንብረታቸዉ የሚፈናቀሉ ወገኖች ቁጥር በሚሊዮኖች ሊገመት እንደሚችል እየተነገረ ነዉ።

https://p.dw.com/p/J3ZR
ምስል picture-alliance/ dpa

አንዳንድ የአካባቢ ተፈጥሮ ተቆርቋሪዎችም ለመጀመሪያ ጊዜ በዓለማችን ከጦርነት ለመሸሽ ከተፈናቀሉ ሰዎች የበለጠ ቁጥር ያለዉ ህዝብ በተፈጥሮ ቁጣ ምክንያት ከአካባቢዉ ተፈናቅሎ ቤት አልባ ይሆናል የሚለዉ ስጋታቸዉ አይሏል። የተመድ የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን እንደሚገምተዉ በመጪዉ የአዉሮጳዉያኑ 2050ዓ,ም ከ200-250 ሚሊዮን የሚገመቱ የተፈጥሮ ቁጣ ያፈናቀላቸዉ ወገኖች ምድራችንን ያጨናንቋታል። የአየር ጠባይ ለዉጥ እጅግ ከሚያሰጓቸዉና ጉዳቱም እየደረሰባቸዉ ከሚገኙ አካባቢዎች የሞልዴቭ ደሴቶች የመጀመሪያ መሆናቸዉ ይነገራል። እንደዉም በአንዳንዶቹ ደሴቶች ላይ የሚገኙት ኗሪዎች አንድ ቀን አገራቸዉ እንዴት ከምድረ ገፅ ልትሰወር እንደምትችል መመልከት ችለዋል። ስጋት የጠናበት መንግስት ታዲያ ከቱሪዝም በሚገኘዉ ጠቀም ያለ ገንዘብ ከወዲሁ ከሲሪላንካ፣ ኢንዶኔዢያና ህንድ መሬት ለመግዛት አስቧል። ላፍታ ወደሞልዲቭ ደሴቶች እናቅና።

ሸዋዬ ለገሠ/ ተክሌ የኋላ