1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሞስኮ-ሩሲያ የፍርድ ቤቱን ዉሳኔ ነቀፈች

ማክሰኞ፣ ነሐሴ 17 2008

የሩሲያ አካል ጉዳተኛ አትሌቶች በቅርቡ ሪዮ በሚደረገዉ የዓለም Paralympics ዉድድር ላይ እንዳይሳተፉ ዓለም አቀፉ የስፖርት ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት መወሰኑን ሩሲያ አጥብቃ ተቃወመች።

https://p.dw.com/p/1Jns7
Brasilien - Paralympics 2016 Fotomontage Flaggen Russland und Paralympische Spiele
ምስል picture-alliance/CITYPRESS24

የሩሲያ አትሌሎች በመንግሥት ድጋፍ ሐይል ሰጪ ንጥረ-ነገር ይወስዳሉ በማለት በዉድድሩ እንዳይካፈሉ የዓለም ፓራሊምፒክስ ኮሚቴ (IPC) ከሁለት ሳምንት በፊት ወስኖ ነበር።ዉሳኔዉን በመቃወም ሩሲያ ይግባኝ የጠየቀችበት ፍርድ ቤት ዛሬ ይግባኙን ዉድቅ አድርጎ የ IPCን ዉሳኔ እንዲፀና በይኗል።የሩሲያዉ ጠቅላይ ሚንስትር ዲሚትሪ ሜድቬዴቭ የፍርድ ቤቱን ዉሳኔ በመላዉ አካል ጉዳተኞች ላይ የተቃጣ ወንጀል በማለት አዉግዘዉታል።ጠቅላይ ሚንስትሩ አክለዉ እንዳሉት የፍርድ ቤቱ ዉሳኔ 80 በመቶ ፖለቲካን፤ 20 በመቶ ደግሞ ሐይል ሰጪ ንጥረ ነገርን መሠረት ያደረገ ነዉ።በዚሕ ዉሳኔ መሠረት ከ250 የሚበልጡ የሩሲያ አካል ጉዳተኛ አትሌቶች ጳጉሜ ማብቂያ በሚጀመረዉ ዉድድር ላይ አይካፈሉም።

ነጋሽ መሐመድ

አዜብ ታደሰ