1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሞዛምቢክን ያሰጋው ቀውስ

ሰኞ፣ ጥቅምት 18 2006

በሞዛምቢክ እአአ ከ1976 እስከ 1992 ዓም በገዢው ፓርቲ ፣ ፍሬሊሞ እና በተቀናቃኙ ሬናሞ መካከል የተከሄደው የርስ በርስ ጦርነት ካበቃ ከ21 ዓመት በኋላ በቀድሞዎቹ ተቀናቃኝ ወገኖች መካከል ውጥረቱ እንደገና እየተካረረ መጥቶዋል።

https://p.dw.com/p/1A6fv
Mozambique's President Armando Guebuza (L) greets solders in Sofala on October 24, 2013. Guebuza called for dialogue on October 24, warning of a threat to peace after two days of tit-for-tat violence between government forces and members of former rebel group Renamo. The two sides signed a peace agreement two decades ago, ending a long civil war, but Renamo declared that accord over after the army seized its base during a raid on October 21. AFP PHOTO / FERHAT MOMADE (Photo credit should read FERHAT MOMADE/AFP/Getty Images)
ምስል Ferhat Momade/AFP/Getty Images

ይህን ተከትሎም የሬናሞ መሪ አፎንዞ ድላካማ ከአንድ ዓመት በፊት በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ታጣቂዎችን ይዘው ወደ ማዕከላይ ሞዛምቢክ በጎሮንጎዛ ተራራማ አካባቢ ወደሚገኘው ሳቱንጂራ በመሄድ በዚያ መሽገዋል። ይኸው ቦታ እንደሚታወሰው በርስበርሱ ጦርነትም ወቅት የሬናሞ ጦር ሠፈር በመሆን አገልግሎዋል። ባለፉት ጥቂት ጊዚያት በተቀናቃኞቹ መካከል በርካታ ግጭቶች ከተፈጠሩ በኋላ የሬናሞ አባላት እአአ በ1992 ዓም የተፈረመው የሰላም ውል እንዳከተመለት በሣምንቱ መጀመሪያ ላይ አስታውቀዋል። ለዚሁ የሬናሞ ውሳኔ የመንግሥቱ ወታደሮች የሰላሙን ውል በመጣስ የሬናሞን የጦር ሠፈር በቦምብ አጥቅተው መያዛቸው ተጠያቂ መሆኑን የሬናሞ ቃል አቀባይ ፌርናንዶ ማዛንጋ አስረድተዋል።
« የሀገሪቱን ጦር ጥቃት ተከትሎ የሬናሞ መሪ አፎንዞ ድላካማ ለሕይወታቸው በመታገል ላይ ይገኛሉ። በዚህም የተነሳ የሰላሙ ውል እንዳከተመለት ለዓለም መግለጽ እንፈልጋለን። »
ማዛንጋ እንዳስረዱት፣ እርግጥ፣ ድላካማ የመንግሥቱን ጥቃት ቢያመልጡም፣ ጥቃቱ በሬናሞ ላይ ጦርነት የማወጅ ያህል ተቆጥሮዋል። ለዚሁ የመንግሥቱ ጥቃት ሬናሞ በወሰደው አፀፋ ርምጃ ባለፈው ማክሰኞ አንድ የፖሊስ ጣቢያ ማጥቃቱ ይታወሳል።
በዚህ በተያዘው አውሮጳዊ ዓመት ብዙ ጊዜ ወደ ሞዛምቢክ የተመላለሱት ጀርመናዊው የልማት ርዳታ አማካሪ ራይነር ቱምፕ እንደጠቆሙት፣ ሬናሞ ባለፉት ጊዚያት በሀገሪቱ የፖለቲካ መድረክ የያዘው ተሰሚነት እየቀነሰ በመሄዱ ለአሁኑ ወዝግብ ምክንያት ሳይሆን አልቀረም።
« ሬናሞ ባለፉት ጊዚያት ጥቃት ወደመሰንዘሩ የዞረበት ዋናው ምክንያት በብሔራዊውም ሆነ በከተሞች ምክር ቤታዊ ምርጫዎች ላይ የተሳካ ውጤት ማግኘት ባለመቻሉ ነው። »
በሞዛምቢክ የርስበርሱን ጦርነት ያበቃው የሰላም ውል የተፈረመበት 20ኛ ዓመት እአአ ጥቅምት 2012 ዓም ከታሰበ ወዲህ በትልቁ የሀገሪቱ የተቃውሞ ፓርቲ «ሬናሞ» እና በገዢው ፓርቲ «ፍሬሊሞ» መካከል ውዝግቡ ተባብሶዋል። የ«ሬናሞ» ተዋጊዎች ባለፈው ሚያዝያ ወር በማዕከላይ የሀገሪቱ ከፊል በሚገኘው የሶፋላ ግዛት አንድ የፖሊስ ጣቢያን አጥቅተው አምስት ሰዎችን ገድለዋል፣ ከዚህ ሌላም በጦር ኃይሉ ከለላ የሚሰጣቸው የተሽከርካሪዎች አጀብ በሚተላለፉበት ሰሜን እና ደቡቡን የሀገሪቱን አካባባዎች በሚያገናኘው መንገድ ላይ በአንድ አውቶቡስ እና አንድ የጭነት ተሽከርካሪ ላይ በጣሉት ጥቃት ሁለት ሲቭሎችን ገደለዋል። ማላዊን እና የሞዛምቢክ ወደብ ከተማ ቤይራን የሚያገናኘው «ቴቴ ራን» በመባል የሚታወቀው እና በርስ በርሱ ጦርነት ጊዜ በጣም አደገኛ የነበረው መንገድ ዛሬም ለሬናሞ ዓማፅያን ጥቃት የተጋለጠ ሆኖዋል። በዓለም ፈጣን ዕድገት እያሳዩ ካሉት ሀገራት መካከል የምትቆጠረው ሞዛምቢክ ምጣኔ ሀብት በዓመት ሰባት ከመቶ ዕድገት ያስመዘገበች ሲሆን፣ ይኸው ዕድገትዋ አሁን በተፈጠረው ውዝግብ ትልቅ ጉዳት ሊደርስበት እንደሚችል አስግቶዋል። ጉዳቱ በተለይ በቴቴ ግዛት በከሰል ድንጋይ ማዕድን ተቋማት ላይ ገንዘባቸውን ያሰሩ ባለወረቶችን ሊነካ ይችላል። ራይነር ቱምፕ እንዳስረዱት፣ ተቋማቱ ምርታቸውን ለንግድ ወደ ውጭ የሚልኩት የሬናሞ ጠንካራ ሠፈር በሆነው በሶፋላ ግዛት በኩል በሚያልፉት መንገዶች እና የባቡር መስመሮች በኩል ነው።
እንደሚመስለኝ ፣ ሬናሞ የጦር ሠፈሩ በመንግሥት በተያዘበት ድርጊት አንድም በጣም ተዳክሞ እና ተከፋፍሎ አንድ ጠንካራ ኃይል ማቋቋም የማይችልበት ደረጃ ላይ ደርሶዋል፤ ወይም ዋናው መተላለፊያ መንገድ በሚገኝበት በሶፋላ ግዛት በሚቀጥሉት ሣምንታት ጥቃቱን አጠናክሮ በዚያ በሚሰሩት ዋነኛ የገቢ ምንጭ በሆኑት የድንጋይ ከሰል ተቋማት ላይ ትልቅ ችግር ሊያስከትል ይችላል። የሞዛምቢክ ሁኔታ እየተበለሸ ከሄደ እነዚህ ተቋማት መስራት አይችሉም፤ ካልሰሩ ደግሞ ከትላልቅ ባንኮች ያገኙትን ብድር መልሰው መክፈል አይችሉም። ይህም ግዙፍ ችግር ይፈጥርባቸዋል ብየ እገምታለሁ። »
ሬናሞ የፍሬሊሞ ፓርቲ ተፅዕኖ በመንግሥቱ ተቋማት ላይ የተጠናከረበትን ድርጊት በጥብቅ በመንቀፍ በሀገሪቱ የፖለቲካ ውሳኔዎች ላይ በይበልጥ ተሳታፊ መሆን እንዳለበት ነው ያስታወቀው። የፊታችን ህዳር ለሚካሄደው የከተሞች ምክር ቤታዊ ምርጫ የሁለቱ ትላልቅ ፓርቲዎች በአስመራጩ ኮሚሽን ውስጥ እኩል ውክልና እንዲያገኙ ያቀረበውን ጥያቄ ፍሬሊሞ እና ከሬናሞ የተገነጠሉ ትናንሾቹ ፓርቲዎች የተቃወሙበት እና ይህን ተከትሎ ሬናሞ ራሱን ከምርጫው ያራቀበት ድርጊት ለውጥረቱ መካረር ድርሻ አበርክቶዋል። በሀገሪቱ በተካሄዱ ምርጫዎች ወቅት በተደረጉ ያልተስተካከሉ አሰራሮች ሬናሞ በተደጋጋሚ ችግር እንዳጋጠመው ራይነር ቱምፕ ገልጸዋል። የሀገሪቱ ዜጎች ሬናሞ ካለፉት ጊዚያት ወዲህ አሰከፊ ጥቃቶች መፈፀሙን በጥብቅ ቢነቅፉም፣ ወደዚሁ ተግባር የተገፋፋበትን ምክንያት እንደሚረዱለት መግለጻቸውን ራይነር ቱምፕ በመገረም ነው ያዳመጡት። እንደ ጀርመናዊው ቱምፕ ግምት፣ ሞዛምቢክ አሁን ለምትገኝበት ሁኔታ ፕሬዚደንት አርማንዶ ገቡዛ ተጠያቂ ናቸው። እአአ ገቡዛ ከ2005 ዓም ወዲህ ሀገሪቱን መምራት ከጀመሩ ወዲህ በመንግሥት ተቋማት ላይ የፍሬሊሞ ተፅዕኖ ከፍ ብሎዋል። የመንግሥት ሰራተኞች የገዢው ፓርቲ አባላት እንዲሆኑ ይገደዳሉ። የመገናኛ ብዙኃንም ለጥንካራ ቁጥጥር ተጋልጠዋል። እነዚህን ወቀሳዎች ያቀረቡት የሬናሞ አባላት ብቻ ሳይሆኑ የሲቭል ማህበረሰቦችም ጭምር ናቸው።

የሞዛምቢክ መንግሥት አሁን በሬናሞ መሪ አፎንዞ ድላካማ ላይ ጥቃቱን ማጠናከሩ በሀገሪቱ ቁጥጥሩን ለማሳደግ ሳይሆን እንዳልቀረ የኦንላይን ጋዜጠኛ ርዊ ላማርኬስ ገምቶዋል፣ ድላካማ ቢገደሉ ሬናሞ እንደሚበታተን እና በአንጎላ ያለውን ዓይነት ንዑሱ ነፃነት ያለበት ሁኔታ ሊፈጠር እንደሚችል የሰጋው ላማርኬስ፣ በሞዛምቢክ ያሉት ንዑሳኑ ፓርቲዎች ወይም አዲስ የሚቋቋሙት ፓርቲዎች የሬናሞን ያህል ፍሬሊሞን ሊቋቋሙ አይችሉም ነው የሚለው፣ ምክንያቱም የሬናሞን ያህል ድጋፍ የላቸውም፣ አይኖራቸውም።
ናሞ እና ፍሬሊሞ በ 1992 ዓም በሮም የተፈራረሙት እና አሁን ሬናሞ አከተመለት ያለውን የሰላም ውል ላይ በአደራዳሪነት የሰራው በሞዛምቢክ የካቶሊካውያኑ የቅዱስ ኤጊዶ ማህበረ ስብ ተወካይ የሆኑት ካርላ ቱሪን ለውዝግቡ በውይይት እንደሚፈታ ተስፋቸውን ገልጸዋል።
« ሁለቱ ወገኖች ለሀገራቸው ሲሉ ለችግራቸው በውይይት መፍትሔ እንደሚያገኙለት ተስፋ አደርጋለሁ። ማንም በሞዛምቢክ ጦርነት እንዲነሳ ይፈልጋል ብየ አላምንም። እንደሚመስለኝ፣ ሕዝቡ 20 ዓመት የዘለቀውን ሰላም ወዶታል። ተቀናቃኞቹ ወገኖች ውይይት መጀመር የሚችሉበትን መንገድ ማግኘት አለባቸው። ምክንያቱም ከጦርነት የምናገኘው ጥቅም የለምና። »


ዮሀንሰ ቤከ/አርያም ተክሌ

epa03919439 Locals flee Maringue after an attack by gunmen on a local police station in Maringue, central Mozambique, 22 October 2013. The incident came after government forces had reportedly attacked the base of Mozambique's opposition Renamo movement leader Afonso Dhlakama, thereby ending an over 20-year-long running peace agreement. EPA/ANDRE CATUEIRA
ምስል picture-alliance/dpa
A picture taken on October 17, 2013 shows prisoners belonging to former Mozambican rebel movement Renamo sitting on the ground with government soldiers guarding them in Gorongosa. Mozambique ex-rebel group Renamo has declared on October 21, 2013 the end of a peace deal signed 21 years ago after the army seized its military base. A spokesman for Renamo, Mozambique's main opposition party, accused the army of trying to kill the group's president Afonso Dhlakama, and said the deal that ended the country's 16-year civil war was over. AFP PHOTO / MARIA CELESTE MAC' ARTHUR (Photo credit should read MARIA CELESTE MAC' ARTHUR/AFP/Getty Images)
ምስል Maria Celeste Mac' Arthur/AFP/Getty Images

ልደት አበበ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ