1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሣዑዲ ዓረቢያ ኢትዮጵያውያን ተመላሾች

ዓርብ፣ ሚያዝያ 6 2009

የሣዑዲ ዓረቢያ መንግሥት ሕገወጥ ያላቸው የውጭ ሃገራት ዜጎች ያለምንም እንግልት እና ቅጣት ሀገር ለቀው እንዲወጡ በሰጠው የ90 ቀናት የምህረት ጊዜ ገደብ ውስጥ ወደ ሀገር ለመመለስ የተመዘገቡ ኢትዮጵያውያን የሚፈለገውን ያህል እንዳልሆነ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር አስታወቀ።

https://p.dw.com/p/2bFkT
Saudi Arabien Arbeiter kehren nach Äthiopien zurück
ምስል DW/S. Shiberu

Ber. A.A. (Saudi Arabia reternee registration is low) - MP3-Stereo

የሣዑዲ ዓረቢያ መንግሥት ከመጋቢት 20 ቀን 2009 ዓ.ም. ጀምሮ በሚጸናው አዋጁ ሕገወጥ ያላቸው የውጭ ሃገራት ዜጎች ያለምንም እንግልት እና ቅጣት ሀገር ለቀው እንዲወጡ የ90 ቀናት የምህረት ጊዜ ሰጥቷል። ኾኖም በዚህ የጊዜ ገደብ ውስጥ ወደ ሀገር ለመመለስ የተመዘገቡ ኢትዮጵያውያን የሚፈለገውን ያህል እንዳልሆነ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር አስታወቀ። የሚንስቴር መሥሪያ ቤቱ ቃል አቀባይ አቶ መለሰ ዓለምን በማነጋገር የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ቀጣዩን ዘገባ ልኮልናል። 

የሣዑዲ ዓረቢያ መንግሥት ሕጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ ሳይኖራቸው በሀገሪቱ የሚኖሩ የውጭ ሃገራት ዜጎች ያለምንም ቅጣት እና እንግልት ከግዛቱ እንዲወጡ የ90 ቀናት ቀነ ገደብ ካስቀመጠ 16 ቀናት ተቆጥረዋል።

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ኂሩት መለሰ