1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ረመዳን ከሪም

ሐሙስ፣ ሐምሌ 25 2005

የረመዳን የጾም ወር ተጋምሶ ፍችዉ የኢድ አልፈጥር በዓል እየተቃረበ ነዉ። በጀርመን የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ሙስሊሞች በቀን ወደ 18 ሰዓት ያህል ይጾማሉ። በዕለቱ ዝግጅታችን በቦን ከተማ አቅራብያ በምትገኘዉ በብሩል ከተማ የሚኖሩ አንድ ኢትዮጵያዊ ሙስሊም ቤተሰብ ቤት ጎራ ብለን የእፈጠር ምሽትን አብረን አሰልፈን ልናካፍላችሁ ይዘናል፤

https://p.dw.com/p/19IEV
Titel: Fastenmonat Ramadan, das Fastenbrechenzeit _Deutsche Brühl, eine muslimische Familie aus Äthiopien Thema: Fastenmonat Ramadan, das Fastenbrechenzeit) 300713 Autor/Copyright: Azeb Tadesse Hahn DW 30072013 Schlagworte: Fastenmonat Ramadan, das Fastenbrechenzeit
ምስል DW/A.Tadesse Hahn

ወ/ሮ ናድያ ያህያ እና አቶ መሃመድ ሄሴን አባዲጋ ዶቼ ቬለ ራድዮ ጣብያ ከሚገኝበት ከቦን ከተማ 25 ኪሎሜትር ርቀት ላይ የምትገኘዉ የብሩል ከተማ ነዋሪ ናቸዉ። ትዳር መስርተዉ የ7 ዓመት ወንድ ልጅና፤ የ5 ዓመት ሴት ልጅ ወላጆችም ናቸዉ። ኢድ አልፈጥር በዓልን ልናከብር አንድ ሳምንት ግድም የቀረዉ የረመዳን ጾም፤ በተለይ በሰሜኑ ንፍቀ ክበብ በሚገኙ ሀገሮች፤ የበጋ ወራት በመሆኑ እና ቀኑ ረዘም ያለ በመሆኑ የረመዳን ጾም እጅግ ከባድ እንደሚደርገዉ ይነገራል። በጀርመን የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ሙስሊሞች፤ የረመዳን ጾምን እንዴት ያሳልፋሉ? የምግብ አሰራሩ፤ የአፈጠር ስነ-ስርዓቱ እና የጸሎት ስነ ስርዓቱ ከኢትዮጵያ ጋር ምን ልዩነት ይኖረዉ ይሆን? ይሄን ጥያቄ ይዘን ለእፍጠር የሚጋብዘን ኢትዮጵያዊን ስናፈላልግ ብዙም ሳንለፋ አገኘን፤ ወ/ሮ ናድያ ያህያን እና አቶ መሃመድ ሄሴን አባዲጋን፤

እፈጠር የምናደርገዉ ከምሽቱ 3 ሰዓት ተኩል ማለትም( በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር 4 ሰዓት ተኩል መሆኑ ነዉ ) በመሆኑ ከምሽቱ ሶስት ሰዓት ላይ እቤታቸዉ እንደሚጠብቁን ነግረዉ የመኖርያ አድራሻቸዉን ሰጡን፤ አቶ መሃመድ ሁሴን ጀለብያ ለብሰዉ ከዉጭ ነበር የተቀበሉን፤ አብሮአቸዉ አንድ ወጣት ጀርመን ነበር፤ እሱም እንደኛዉ ከቤተሰቡ ጋር ለማፍጠር ተጋብዞ ነበር የመጣዉ፤ ወ/ሮ ናድያ ያህያ፤ የዶሮ ጥብስ የስጋ፤ ጥብስ ድንች ብስኩት ሳንቡሳ፤ የሚጠጣዉ የፍራፍሪ ጭማቂና የተለያየ ፍራፍሪ ፤እንጀራ፤ በምግብ ጠረቤዛዉ ላይ ደርድረዉ እየጠበቁን ደረስን ገብተን ቁጭ ከማለታችን ከምሽቱ ሶስት ሰዓት ተኩል ግድም ሆነና፤ ለእፈጠር ወደተዘጋጀዉ ጠረቤዛ ሄድን፤ አቶ መሃመድ ሁሴን ፤ ስነ-ስርዓቱን በጸሎት ጀመሩ፤ እፈጠር ስነ-ስርዓቱ ቴምር በመብላት ነበር የተጀመረዉ፤ በመለጠቅ ሾርባ ለምን? እቤት ዉስጥ ከወይዘሮ ናድያ ያህያ ጋር ጓዳ ጉድ ጉድ ሲሉ የነበሩ የዚሁ ከተማ ነዋሪዋ ኤርትራዊት ወ/ሮ አበባ ነበሩ፤ ወሮ አበባ ከአስር ዓመታት በላይ ሳዉዲ በመኖራቸዉ፤ አርብኛ ይናገራሉ፤

Titel: Fastenmonat Ramadan, das Fastenbrechenzeit _Deutsche Brühl, eine muslimische Familie aus Äthiopien Thema: Fastenmonat Ramadan, das Fastenbrechenzeit) 300713 Autor/Copyright: Azeb Tadesse Hahn DW 30072013 Schlagworte: Fastenmonat Ramadan, das Fastenbrechenzeit
ምስል DW/A.Tadesse Hahn

የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይም ቢሆኑ፤ በተለይ በተለይ ረመዳንን እጅግ እንደሚወዱ፤ በሳዉዲ ያዩትን ደማቅ የረመዳን አከባበር በማስታወስ ይናገራሉ፤ በዚሂም ረመዳንን እዚህ ከወ/ሮ ናድያ ጋር በጋራ ነዉ የሚያሳልፉት፤ ሌላዉ የእስልምና ሃይማኖትን መከተል ከጀመረ ሁለት ዓመት ግድም እንደሆነ የሚገልጸዉ የ19 ዓመቱ ጀርመናዊ ቢላል፤ የረመዳን ጾምን ሲያከብር ዘንድሮ ሁለተኛ ዓመቱን ይዞአል፤ በገበታ ሳለን የጸሎት ስርዓቱን ሁሉ በስነ ስርአት ያዉቃል በረመዳን ጾም ወቅት ይላል ቢላል፤ « አንድ ሰዉ በረመዳን ጾም ወቅት ጥሩ ነገርን ሰርቶ ለማለፍ መሞከር ይኖርበታል። በረመዳን ጾም ምግብን ሳይመገቡ መዋል ብቻ ሳይሆን ጥሩ ያልሆነ ነገር ሁሉ ከመስራት መቆጠብ ተገቢ ነዉ» መቅረፀ ድምጼን በአንድ እጄ ይዤ፤ በሌላ እጄ ሳንቡሳን እየበላሁ፤ እኔም ተሰለፍኩ፤ ከጾመኞቹ እኩል፤ ይሄ ሁኔታ ያኔ በልጅነቴ ጎረቤታችን ለረመዳን ጾም፤ ለኢድ አልፈጥር በዓል የሚሰጡን ሳንቡሳና ጣፋጭ ትዝ አሰኘኝ። ብዪ እንጂ የተለመደ የኢትዮጵያዊ መስተንግዶ ነዉ። በህጻንነት የሰፈሩ ህጻን ሁሉ ረመዳን እና ኢድ መጥቶ ሳንቡሳ ያግኝ እንጂ ስለረመዳን ምንነት ጠልቆ የሚጠይቅ አልነበረም። ለሙስሊሞች የረመዳን ጾም ምንድን ነዉ? ረመዳን መጣ ሲባል ለኢትዮጵያ ሴቶች ድካም ነዉ ይባላል። ቤት ማጽዳቱ፤ የተለያየ ምግብን ማዘጋጀቱ ልጆች ላሉዋቸዉ እናቶች ከባድ መሆኑ ነዉ የሚነገረዉ። በጀርመንስ ይህ ሁኔታ እንዴት ይሆን ወይዘሮ ናድያ ያህያ በጀርመን ይላሉ፤ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች በሃይማኖታቸዉ ጉዳይ ጣልቃ ይገባል ያሉት የሀገሪቱ መንግስት በተለያዩ መንገዶች እየተቃወሙ ነዉ። በዚህ በጾም ሰዓት ኢትዮጵያ ዉስጥ ያለዉን ሁኔታ በጀርመን የሚገኙ ሙስሊሞችም ከጎን እንደቆሙ አቶ መሃመድ ሁሴን ተናግረዋል። በጠረቤዛዉ ሙሉ የቀረበዉን፤ የተለያየ ምግብ አይነት ከየዓይነቱ እያወጣን በልተን፤ በመሃል ለጸሎት ለትንሽ ደቂቃዎች እየተለዩን፤ ቡናም በኢትዮጵያ ባህል ተቆልቶ፤ተወቅጦ እና በጀበና ቀርቦ፤ እጣኑ ተጨሶ፤ አቦል ጠጣንና ሰዓት አየን፤ ከለሊቱ ሰባት ሰዓት ይላል፤ ደህና እደሩ ልሂድ አልኩ፤ እነሱ ገና እስከ ለሊቱ አስራ አንድ ሰዓት እንደሚቆዩ ነግሩኝ፤ ሳንቡሳ ተሰቶኝ ረመዳን ከሪም ብዪ አመስግኜ ወጣሁ፦ ሙሉዉን ቅንብር የድምፅ ማድመጫዉን ምስል በመጫን ይከታተሉ።

አዜብ ታደሰ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ