1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

እጩ ራይላ ኦዲንጋ ራሳቸውን ከፕሬዚደንታዊው ምርጫ ማግለል

ማክሰኞ፣ መስከረም 30 2010

የኬንያ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ህብረት፣ በምህጻሩ የናሳ እጩ ራይላ ኦዲንጋ በጎርጎሪዮሳዊው የፊታችን ጥቅምት 26፣ 2017 በሚደረገዉ ድጋሚ ፕሬዝደንታዊ ምርጫ እንደማይወዳደሩ ዛሬ አስታወቁ።

https://p.dw.com/p/2lbBP
Kenia Nairobi Opposition ehemailger Präsident Raila Odinga
ምስል Reuters/B. Ratner

ራይላ ኦዲንጋ በፕሬዚደንታዊው ምርጫ አልወዳደርም አሉ።

ኦዲንጋ በሀገሪቱ አስመራጭ ኮሚሽን ላይ  እና በምርጫ ሕጉ ላይ ለውጦች እና ማሻሻያዎች እንዲደረጉ ከመጀመሪያው ፕሬዚደንታዊ ምርጫ ሂደት ወዲህ ያቀረቡዋቸው ጥያቄዎች የሚጠብቁትን መልስ ካላገኙ በድጋሚው ምርጫ እንደማይሳተፉ ያሰሙትን ዛቻ አሁን በዚሁ ውሳኔአቸው እውን አድርገውታል። ይኸው የራይላ ኦዲንጋ ውሳኔ ለመጻዒው ፕሬዚደንታዊ ምርጫ ምን ተፅዕኖ ይኖረዋል?  ሸዋዬ ለገሠ ናይሮቢ የሚገኙትን አቶ ፍቅረማርያም መኮንንን በስልክ አነጋግራቸዋለች።

ሸዋዬ ለገሠ

አርያም ተክሌ