1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሰላማዊ ሰልፍ በብራስልስ

ዓርብ፣ ግንቦት 26 2008

የአዉሮጳ ኅብረት ኢትዮጵያ ዉስጥ በኦሮሞ ተወላጆች ላይ ይፈጸማል ያለዉን የመብት ጥሰት አስመልክቶ ከወራት በፊት ያሳለፈዉን ዉሳኔ ተግባራዊ እንዲያደርግ ተጠየቀ።

https://p.dw.com/p/1J09R
Brüssel Europäische Kommission Außenansicht
ምስል picture-alliance/dpa/D. Kalker

[No title]

ዛሬ ብራስልስ ቤልጅየም ከሚገኘዉ የኅብረቱ ጽሕፈት ቤት ፊት ለፊት ለሰላማዊ ሰልፍ የወጡት ኢትዮጵያዉያን አሁንም በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች ግድያ፣ እሥራት፣ እና ማዋከብ ይፈጸማል ሲሉ ድርጊቱን አዉግዘዋል።

በሰልፉ ላይ ከቤልጅግ፤ ከጀርመን፤ ከፈረንሳይ፤ ከሆላንድ፤ ከጣሊያን፣ ከስዊድንና ከሌሎችም የአዉሮጳ ሃገራት የመጡ ወገኖች መገኘታቸዉን ተገልጿል። ሰላማዊ ሰልፈኞቹ በተወካዮቻቸዉ አማካኝነት አቤቱታቸዉን በደብዳቤ አስፍረዉ ለአዉሮጳ ኅብረት የዉጭ ግንኙነት ጽሕፈት ቤት ማቅረባቸዉን ሰልፉን ተገኝቶ የተመለከተዉ የብራስልስ ዘጋቢያችን ገበያዉ ንጉሤን ገልጾልናል።

ሸዋዬ ለገሠ/ገበያዉ ንጉሤ

አርያም ተክሌ