1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሰማያዊ ፓርቲ ለሜርክል የላከዉ ደብዳቤ

ሰኞ፣ ሰኔ 1 2007

የሰባቱ የበፀጉት ዓለም ሃገራት የወቅቱ ሊቀመንበር ጀርመን በባቫርያ ግዛት ላይ በተካሄደዉ ጉባኤ ላይ የጀርመንዋ መራሂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል፤ የኢትዮጵያዉን ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝን መጋበዛቸዉን በመቃወም የኢትዮጵያ መንግሥት ተቃዋሚ ሰማያዊ ፓርቲ ለመራሂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል ግልፅ የተቃዉሞ ደብዳቤ አቀረበ።

https://p.dw.com/p/1FdZ5
Pressekonferenz Äthiopien Parteien,
ምስል DW

[No title]


የፓርቲዉ ሊቀመንበር ኢንጂኔር ይልቃል ጌትነት እንደተናገሩት ደብዳቤዉ መራሂተ መንግሥቷ እጅ ደርሷል።
ትናንት አረፋፈዱ ላይ ጀርመን ባቫርያ ግዛት በሚገኘዉ «ኤልማዉ» ጥንታዊ ቤተ-መንግሥት ዉስጥ ጉባኤያቸዉን ጀመሩት ሰባቱ በኢንዱስትሪ የበለፀጉት ሃገራት መሪዎች ዛሬ በሁለተኛዉ ቀን ጉባኤያቸዉ ላይ ከአፍሪቃ የኢትዮጵያዉን ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝን ጨምሮ አምስት መሪዎችን ጋብዘዋል።

የቡድን ሰባት የወቅቱ ሊቀ-መንበር የጀርመኗ መራሂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል የኢትዮጵያዉን ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝን በዚህ ጉባኤ መጋበዛቸዉ እጅግ አሳዝናል ያለዉ የኢትዮጵያ መንግሥት ተቃዋሚ «ሰማያዊ ፓርቲ» ለመራሂተ መንግሥትዋ ግልፅ ደብዳቤን ጽፎአል። የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢንጂኔር ይልቃል ጌትነት እንደሚሉት ግብዣዉ በኢትዮጵያ ያለዉን ሁኔታ ግምት ዉስጥ ያላስገባ ነዉ።


በሃገሪቱ ነፃና ትክክለኛ ምርጫ አልተካሄደም፤ ለ 24 ዓመታት ስልጣን ላይ የሚገኘዉ መንግሥት አሁንም በርካቶችን በእስር በመያዙ ለከፍተኛ ባለስልጣናቱ በዚህ ደብዳቤ ጥያቄያችንን አቅርበናል ሲሉ ኢንጂኔር ይልቃል ጌትነት ተናግረዋል።
ሰማያዊ ፓርቲ ለጀርመንዋ መራሂተ መንግሥት ከላከዉ ደብዳቤ መልስ ይገኛል ብሎ ይጠብቅ ይሆን፤ ይህ በነሱ በኩል የሚታይ ይሆናል። እዉነታዉ ሁሉ ነገር መሸፋፈን በማይቻልበት አኳን ይፋ ወጥቷል ሲሉ የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢንጂኔር ይልቃል ጌትነት መልስ ሰጥተዋል።


አዜብ ታደሰ
ነጋሽ መሃመድ